1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የተፈታኞች ዝግጅት በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ

እሑድ፣ መስከረም 29 2015

ነገ ሰኞ የሚጀመረውን ፈተና ለመውሰድ ከተለያዩ አካባቢዎች በመነሳት በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የሚገኙ ተማሪዎች የፈተናውን ሚሥጢራዊ ደህንነት ለመጠበቅ በሚንስትሩ የተከናወኑ ሥራዎችን በበጎ ጎን እንደሚመለከቱት ይናገራሉ ፡፡

https://p.dw.com/p/4HxKk
Äthiopien Studenten bereiten sich an Universität Hawasa auf Prüfung vor
ምስል Shewangizaw Wegayoh/DW

የተፈታኞች ዝግጅት በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ

 የዘንድሮው የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ መልቀቂያ ፈተና ተፈታኞች  ከባለፈው ዓርብ ጀምሮ ወደ ዩኒቨርሲቲዎች እየገቡ የሚገኙ ሲሆን ከነገ ሰኞ ጀምሮ ደግሞ ፈተናዎቹን መውሰድ ይጀምራሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡ የትምህርት ሚኒስቴር ሚንስትር ፕሮፌሰር ብረሃኑ ነጋ ፈተናዎችን በዩኒቨርስቲዎች መስጠት ያስፈለገው የፈተናውን ምሥጢራዊ ደህንነት እንዲጠበቅ ለማድረግ መሆኑን ከቀናት በፊት ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ ማስታወቃቸው ይታወቃል፡፡
ነገ ሰኞ የሚጀመረውን ፈተና ለመውሰድ ከተለያዩ አካባቢዎች በመነሳት በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የሚገኙ ተማሪዎች የፈተናውን ሚሥጢራዊ ደህንነት ለመጠበቅ በሚንስትሩ የተከናወኑ ሥራዎችን በበጎ ጎን እንደሚመለከቱት ይናገራሉ ፡፡ ለዶቼ ቬለ DW አስተያየቱን የሰጠውና ከሶማሌ ክልል ዳዋ ዞን መምጣቱን የሚናገረው ሰላድ ኢብራሂም ፈተናውን በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ውስጥ ለመውሰድ በመምጣቱ  ደስተኛ መሆኑን ገልጿል ፡፡ ወደ ግቢው ይዘን እንድንገባ የተፈቀደልን እስኪርብቶ ብቻ ነው የሚለው ሳላድ ‹‹ ይህም ከዚህ በፊት በተንቀሳቃሽ ስልኮች አማካኝነት ይደረግ ነበረውን የመልስ መቀባበል ለማስቀረት ያግዛል የሚል እምነት አለኝ ›› በሏል፡፡ከደቡብ ክልል ዳውሮ ዞን የመጣችሁ ደመች ታደለ በሰላድ ሀሳብ እንደምትስማማ ትናገራለች ፡፡ ቀደምሲል በነበሩ መደበኛ ፈተናዎች በቴሌግራምና በመሰለ መንገዶች የፈተና ጥያቄዎች ቀደምው በመውጣት  በተፈታኞች እጅ ሲገቡ በተደጋጋሚ መመልቷን የምታስታውሰው ደመቀች ፈተናው በሌላ ቦታ መካሄዱ ይህንን ችግር ያስቀራል ፡፡ እኛም ያለንበትን ትክክለኛ የእውቀት ደረጃ ለማወቅ ያስችለናል ›› ብላለች ፡፡
አሁንባለው ሁኔታ አብዛኞቹ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ፈተናውን በነገው ዕለት ለመጀመር የሚስችላቸውን መሰናዶ ማጠናቀቃቸውን እየገለጹ ይገኛሉ፡፡ አቶ ተመስገን ከበደ በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የተማሪዎች አገልግሎት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ናቸው ፡፡ አቶ ተመስገን ዩኒቨርሲቲያቸው በሁለት ዙር ከ52 ሺህ በላይ ተማሪዎችን ተቀብሎ እንደሚያስተናግድ ይናገራሉ ፡፡ የፈተናው መመሪያ በሚፈቅደው መሠረት የተፈታኝ ተማሪዎችን ቁጥር ታሳቢ ያደረገ የመፈተኛ ክፍሎች  መመቻቸታቸውን የጠቀሱት አቶ ተመስገን ‹‹ ስምንት የመመገቢያ አዳራሾችና የመኝታ አገልግሎቶችን ጨምሮ ተያያዥ ዝግጅቶች ተደርገዋል፡፡ ዛሬ ላይ ሁሉም ተፈታኞች ወደ ግቢው በመግባታቸው የቅበላውን ምዕራፍ  አጠናቀናል ፡፡ ቀሪው በየዕለቱ ፈተናዎቹን የመስጠቱ ሥራ ይሆናል ›› ብለዋል፡፡
በዘንድሮው የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ መልቀቂያ ፈተና በሁለት ዙር ከ976 ሺህ በላይ ተማሪዎች ለፈተና ይቀመጣሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ ከትምህርት ሚኒስቴር የተገኘው መረጃ ያመለክታል ፡፡
ሽዋንግዛው ወጋዮህ
ዮሐንስ ገብረእግዚአብሔር

Äthiopien Studenten bereiten sich an Universität Hawasa auf Prüfung vor
ምስል Shewangizaw Wegayoh/DW
Äthiopien Studenten bereiten sich an Universität Hawasa auf Prüfung vor
ምስል Shewangizaw Wegayoh/DW