የተወካዮች ም/ቤት 6ኛው ሀገራዊ ምርጫ እንዲካሄድ ወሰነ
ማክሰኞ፣ መስከረም 12 2013ማስታወቂያ
የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዛሬ ባደረገው አስቸኳይ ጉባዔ ስድስተኛው ሀገር አቀፍ ጠቅላላ ምርጫ በዚህ ዓመት እንዲከናወን ወሰነ።ምክር ቤቱ በዛሬ ውሎው ምርጫውን ከተመለከተው ውሳኔ በተጨማሪ በኮሮና ተኅዋሲ ምክንያት ታግደው የነበሩ ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ መስተጋብሮች ማለትም የሕዝብ ስብሰባዎች፣ ክብረ በዓላት ፣ የስፖርት ፣ የትራንስፖርት እና የቱሪዝም እንቅስቃሴዎች በከፍተኛ ጥንቃቄ ውስጥ ሆነው እንዲከናወኑ በአንድ ተቃውሞና በስምንት ድምፅ ተዓቅቦ በአብላጫ ድምፅ አፅድቋል።በተጨማሪም የሚኒስትሮችንና የፌደራል ፍርድ ቤት እጩ ዳኞችን ሹመትም አፅድቋል።
ሰለሞን ሙጬ
ታምራት ዲንሳ
እሸቴ በቀለ