1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ፈረንሳይ ከአፍሪካ 3ሺህ ስደተኞችን ለመቀበል ተስማማታለች

ማክሰኞ፣ ታኅሣሥ 17 2010

ፈረንሳይ “ስደተኞችን እየተቀበልኩ ነው” ብትልም ሀገሪቱ አዲስ ስደተኞችን እና ተገን ጠያቂዎችን በተመለከተ ያዘጋጀችው ረቂቅ ሕግ ግን ተቃውሞ ገጥሞታል፡፡ የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾች እና እርዳታ ሰጪ ተቋማት ረቂቅ ህጉ “የስደተኞችን መብት የሚገፋ እና ወደ ሀገራቸው እንዲመለሱ የሚያስገድድ ነው” በሚል ነቅፈዉታል።

https://p.dw.com/p/2pxzf
Rettungsaktion von Ärzte ohne Grenzen Mittelmeer
ምስል DW/K. Zurutuza

ፈረንሳይ ከአፍሪካ 3ሺህ ስደተኞችን ለመቀበል ተስማማታለች

የተባበሩት መንግስታት የስደተኞች ከፍተኛ ኮሚሽነር (UNHCR) ወደ አውሮፓ ለመሻገር ሊቢያ ከደረሱ በኋላ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ይገኙ ከነበሩ አፍሪካውያን ስደተኞች መካከል የተወሰኑትን ኒጀር እና ቻድ ወዳሉ የስደተኛ መጠለያ ጣቢያዎች እያዛወረ ነዉ፡፡ ፈረንሳይ በእነዚህ ጣቢያዎች ከሚገኙት መካከል ሶስት ሺህ ስደተኞችን እስከ ጎርጎሮሳዊው 2019 ዓ.ም. ድረስ እንደምትቀበል አስታዉቃለች። የመጀመሪያዎቹን 55 ስደተኞች ባለፈው ሳምንት ፈረንሳይ ደርሰዋል፡፡   

ፈረንሳይ “ስደተኞችን እየተቀበልኩ ነው” ብትልም በስደተኞች አያያዟ ተደጋጋሚ ትችቶች ይቀርብባታል።  ሀገሪቱ አዲስ ስደተኞችን እና ተገን ጠያቂዎችን በተመለከተ ያዘጋጀችው ረቂቅ ሕግም ተቃውሞ ገጥሞታል፡፡ ረቂቅ ህጉ በሀገሪቱ ምክር ቤት ለውይይት ከመቅረቡ በፊት የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾች እና እርዳታ ሰጪ ተቋማት “የስደተኞችን መብት የሚገፋ እና ወደ ሀገራቸው እንዲመለሱ የሚያስገድድ ነው” በሚል ነቅፈዉታል። የፓሪሷ ዘጋቢያችን ሃይማኖት ጥሩነህ የላከቸውን ዝርዝር ዘገባ ለማድመጥ የድምጽ ማዕቀፉን ይጫኑ።  

ሃይማኖት ጥሩነህ

ነጋሽ መሐመድ