1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የተቋማት ስያሜ ለውጥና የሐውልት ነቀላ በአማራ ክልል

ማክሰኞ፣ ታኅሣሥ 13 2013

የአማራ ክልል ባለስጣናትና የፖለቲካ አቀንቃኞች፣ ስም የመለወጥና ሐዉልት የማፍረሱን ዘመቻ ለመክፈታቸዉ የሚሰጡት ምክንያት ለየተቋማቱ የተሰጠዉ ስምና ሐዉልቶቹ የቆሙት በሕዝብ ተሳትፎና ፍላጎት አልነበረም የሚል ነዉ።

https://p.dw.com/p/3n6ht
Äthiopien I Bahir Dar I Statue
ምስል Alemnew Mekonnen/DW

የአማራ ክልል ተቋማት የስም ለዉጥና ሐዉልት ነቀላ

ባለፈዉ ዓመት ብልፅግና ወደሚባል ፓርቲ የተለወጠዉ የኢትዮጵያ ሕዝቦች አብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ  ግንባር (ኢሕአዴግ) ኢትዮጵያን ይገዛ በነበረበት ዘመን በአማራ ክልል ለተቋማት የተሰጡ ስሜዎች እየተቀየሩ፤ የመታሰቢያ  ሐውልቶችም እየተነቀሉ ነዉ።የአማራ ክልል ባለስጣናትና የፖለቲካ አቀንቃኞች፣ ስም የመለወጥና ሐዉልት የማፍረሱን ዘመቻ ለመክፈታቸዉ የሚሰጡት ምክንያት ለየተቋማቱ የተሰጠዉ ስምና ሐዉልቶቹ የቆሙት በሕዝብ ተሳትፎና ፍላጎት አልነበረም የሚል ነዉ።አዳዲሱ ስያሜ ግን የአማራን ታሪክና ሥነልቡና የጠበቀ ነዉ ባዮች ናቸዉ።የስም ለዉጥና የሐዉልት ነቀላዉን «ችኮላና ሩጫ» የሚሉ ወገኖች ግን እርምጃዉን ይቃወማሉ።

ዓለምነዉ መኮንን 

ነጋሽ መሐመድ

ሸዋዬ ለገሰ