1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የተቃዋሚዎች ቅሬታ ለምርጫ ቦርድ

ረቡዕ፣ የካቲት 3 2013

ምርጫ ቦርድ የሚቀርቡለትን ቅሬታዎች በአግባቡ ምልሽ እንዲሰጥ በአንዳንድ ተቃዋሚዎች ተጠየቀ። ቦርዱ ዛሬ ከተቃዋሚ ፓርቲዎች ጋር ባደረገው የምክክር መድረክ እስካሁን የተከናወኑ የዝግጅት ተግባራትን ዘርዝሯል።

https://p.dw.com/p/3pAsu
Äthiopien Addis Abeba | Parteien | ENEBE
ምስል Yohannes Gebreegziabher/DW

ቅሬታዎች በአግባቡ ምልሽ እንዲሰጥባቸው ተጠየቀ

ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የሚቀርቡለትን ቅሬታዎች በአግባቡ ምልሽ እንዲሰጥ በአንዳንድ ተቃዋሚዎች ተጠየቀ። ቦርዱ ዛሬ ከተቃዋሚ ፓርቲዎች ጋር ባደረገው የምክክር መድረክ እስካሁን የተከናወኑ የዝግጅት ተግባራትን ዘርዝሯል። ተቃዋሚዎች በበኩላቸው እስካሁን የተከናወኑ ተግባራትን በማድነቅ በየጊዜው ለሚቀርቡ ቅሬታዎች ፈጣን እና በደብዳቤ ምላሽ አለመስጠቱን ወቅሰዋል። በጽሑፍ ለሚቀርቡ አቤቱታዎች በጽሑፍ ምላሽ አለመሰጠቱን በተመለከተ፦ ቅሬታውን የተቀበሉት የቦርዱ ሰብሳቢ ወ/ት ብርቱካን ሚደቅሳ፦ «ለተፈጠረው ክፍተት ይቅርታ» በመጠየቅ የሚቀርቡ አቤቱታዎች እጅግ መብዛታቸውን ጠቊመዋል።

ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር

ማንተጋፍቶት ስለሺ

ነጋሽ መሐመድ