1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

 የተቃዋሚ ፓርቲዎች ጥያቄ

ረቡዕ፣ ሐምሌ 1 2012

ባልደራስ ለእዉነተኛ ዴሞክራሲ እና አብሮነት ለኢትዮጵያ ፌደራላዊ አንድነት (አብሮነት ባጭሩ) በየፊናቸዉ ባወጡት መግለጫ ከድምፃዊ ሐጫሉ ሁንዴሳ መገደል ለተቀሰቀሰዉ ቀዉስም መንግሥትን ተጠያቂ አድርገዋል።

https://p.dw.com/p/3ez5t
Karte Äthiopien englisch

ተቃዋሚ ፓርቲዎቹ መንግሥትን ወቀሱ

የኢትዮጵያ መንግሥት ባለፈዉ ሳምንት ያሰራቸዉን የሁለት ተቃዋሚ ፓርቲዎች መሪዎች እንዲለቅ፣ ሠብአዊ ክብርና መብታቸዉን እንዲጠብቅም ሁለቱ ፓርቲዎች ጠየቁ።ባልደራስ ለእዉነተኛ ዴሞክራሲ እና አብሮነት ለኢትዮጵያ ፌደራላዊ አንድነት (አብሮነት ባጭሩ) በየፊናቸዉ ባወጡት መግለጫ ከድምፃዊ ሐጫሉ ሁንዴሳ መገደል ለተቀሰቀሰዉ ቀዉስም መንግሥትን ተጠያቂ አድርገዋል።በተለይ አብሮነት ባለፉት ሁለት ዓመት የተደረገዉ ለዉጥ ሐገሪቱን ወደ ተሻለ ሥርዓት ከማሻገር ይልቅ ወደ ባሰ የሕልዉና አደጋ ማስገባቱ ግልፅ ሆኗል ብሏል።

ሰለሞን ሙጬ 

ነጋሽ መሐመድ

አዜብ ታደሰ