1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የተቃዋሚ ፓርቲዎች ዝምታ

ሰኞ፣ የካቲት 9 2012

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ወደሥልጣን ከመምጣታቸው አስቀድሞ በንቃት ይንቀሳቀሱ የነበሩት እነዚህ ፓርቲዎች ባለፉት ጥቂት የማይባሉ ወራት እንቅስቃሴያቸው የተገታ መስሏል።

https://p.dw.com/p/3XnUJ
Äthiopien Stadtansicht Mekele
ምስል DW/M. Hailessilasie

የተቃዋሚ ፓርቲዎች ዝምታ

ኢትዮጵያ ውስጥ ቁጥራቸው የበረከተ የተቃዋሚ ወይም በአዲሱ አጠራር ተፎካካሪ ፓርቲዎች ይገኛሉ። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ወደሥልጣን ከመምጣታቸው አስቀድሞ በንቃት ይንቀሳቀሱ የነበሩት እነዚህ ፓርቲዎች ባለፉት ጥቂት የማይባሉ ወራት እንቅስቃሴያቸው የተገታ መስሏል። ታዛቢዎች አንዳንዶቹም በሀገሪቱ የሚታየው የፀጥታ ስጋትም ሆነ ፖለቲካዊ እና ማኅበራዊ ችግሮች በለውጥ ሂደት የሚከሰቱ ናቸው በሚል ዝምታን መምረጣቸውን ይናገራሉ። በሌላ ወገን ደግሞ ብሔርተኝነትን በይፋ የሚያቀነቅኑ ፓርቲዎች መኖራቸው  ለዘብተኞቹንም ወደእነሱ በመሳብ ትኩረታቸውን እንዳደናገሩባቸውም ያመለከታሉ። በተለይ ሀገር ውስጥ ቆይተው ላለፉት በርካታ ዓመታት የአገዛዙ ጠንካራ መዳፍ ሰለባ የሆኑ ተቃዋሚ ፓርቲዎች መኖራቸው ባይካድም የኅብረተሰቡን ስጋት ለማንፀባረቅ አቅም ያነሳቸው ለምን ይሆን የሚለው ጥያቄ መነሳት ከጀመረ ውሎ አድሯል። የተቃዋሚ ፓርቲዎች ዝምታ ለምን? ሲል ዶይቼ ቬለ እንግዶችን ጋብዞ አወያይቷል።

ሸዋዬ ለገሠ

አዜብ ታደሰ