1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

«የተማሪዎች ዘመቻ ከዓውድ ውጭ ተዘግቧል» የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት

ቅዳሜ፣ ኅዳር 25 2014

መንግሥት የኢትዮጵያን ህልውና የማስጠበቅ ዘመቻ እና ትልእኮን በተሳሳተ ምልኩ ትርጉም በመስጠት ዜጎችንና እና አለምአቀፉ ማህበረሰብን እያደናገሩ ነው ሲል የተወሰኑ ዓለምአቀፍ መገናኛ ብዙኃንን ነቀፈ።

https://p.dw.com/p/43q6f
Karte Äthiopien englisch

የተማሪዎች የሰብል ስብሰባ ዘመቻ ከዓውድ ውጭ መዘገቡን የመንግስት ኮሙኒኬሽን አስታወቀ

መንግሥት የኢትዮጵያን ህልውና የማስጠበቅ ዘመቻ እና ትልእኮን በተሳሳተ ምልኩ ትርጉም በመስጠት ዜጎችንና እና አለምአቀፉ ማህበረሰብን እያደናገሩ ነው ሲል የተወሰኑ ዓለምአቀፍ መገናኛ ብዙኃንን ነቀፈ።
የትምህርት ሚኒስቴር የዘማች ቤተሰቦችን ሰብል ለመሰብሰብ በሚል ተማሪዎች በማህበራዊ አገልግሎቶች ተሳታፊ እንዲሆኑ ለማድረግ የሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎች ለውስን ቀናት ትምህርት እንዲያቆሙ መወሰኑን አንድ አለማቀፍ የመገናኛ ብዙኃን ሽፋን የሰጠበት አውድ ከእውነት የራቀ መሆኑንም አስታውቋል።
በውጪ የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን ለሀገራቸው ድምፅ መሆናቸውን ያደነቀው መንግሥት አንድ ሚሊዮን ዲያስፖራ ወደ አገር እንዲገባ የታቀደውን ውጥን መንግሥት ትልቅ ትርጉም ሰጥቶ ተቀብሎታል በማለት የመንግሥት ኮሙኒኬሽን ዛሬ በሰጠው መግለጫ ተናግሯል።

ሰለሞን ሙጬ

ታምራት ዲንሳ