1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የተመዘበረዉ የመቅደላ ቅርሰን በዉሰት?

ሐሙስ፣ ሚያዝያ 11 2010

አፄ ቴዎድሮስ ሃገሬ በጠላት እጅ አትወድቅም ብለዉ ራሳቸዉን ከሰዉ በኋላ በ1868 ዓ.ም ከመቅደላ አምባ የተዘረፉት ቅርሶች በተለይ ከ500 በላይ የተለያዩ የፈጠራ ውጤቶች ያሉባቸዉ የብራና ጽሑፎች፤ ፤ የንጉሣውያን የወርቅ ዘውዶችና ጌጣ ጌጦች፣ እንዲሁም ወደ አስር የሚሆን የኦርቶዶክስ ሃይማኖት ታቦታት በእንግሊዝ የተለያዩ ሙዚየሞች ይገኛሉ።

https://p.dw.com/p/2wMT2
Äthiopien Tewodros
ምስል Victoria and Albert Museum, London

«የብሪታንያ ፓርላማ ካላፀደቀ ሙዚየሙ በቅሶቹ ላይ መብት የለዉም»

 «እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ ለቅርስ ዋጋ አለመስጠቱ ነዉ እነሱም ለቅርስ ደንታ ቢስ ስለሌለን ነዉ በዉሰት እያሉ የሚቀልሱት» ሲሉ በለንደን የኢትዮጵያ ቅርፅ ማበልጸግያ ማኅበር ሊቀመንበር አቶ አለባቸዉ ደሳለኝ ተናግረዋል። ከ150 ዓመታት በፊት በዳግማዊ አፄ ቴዎድሮስ ዘመን በእንግሊዝ ሠራዊት ከመቅደላ አምባ የተዘረፉት ቅርሶች «ኢትዮጵያ ፍላጎቱ ካላት ለረዥም ጊዜ በውሰት ልንሰጥ እንችላለን» የሚለውን የቪክቶሪያና አልበርት ሙዚየምን መግለጫ፤ ከተሰማ በኋላ በርካታ ኢትዮጵያዉያንን እያስቆጨ እያነጋገረ ያለ ጉዳይ ነዉ። አፄ ቴዎድሮስ ሃገሬ በጠላት እጅ አትወድቅም ብለዉ ራሳቸዉን ከሰዉ በኋላ በ1868 ዓ.ም ከመቅደላ አምባ የተዘረፉት ቅርሶች በተለይ ከ500 በላይ የተለያዩ የፈጠራ ውጤቶች ያሉባቸዉ የብራና ጽሑፎች፤ ፤ የንጉሣውያን የወርቅ ዘውዶችና ጌጣ ጌጦች፣ እንዲሁም ወደ አስር የሚሆን የኦርቶዶክስ ሃይማኖት ታቦታት በእንግሊዝ የተለያዩ ሙዚየሞች ይገኛሉ። ከዚህ በተጨማሪም በርካታ ቅርሶች በግለሰብ እጅ እንደሚገኙ የኢትዮጵያን ቅርስ ከበራሳቸዉ ወጭ ከእንጊሊዞች ላይ እየገዙ በመሰብሰባቸዉ የሚታወቂቁት አቶ አለባቸዉ ደሳለኝ ናቸዉ።

Äthiopien Mekedela
መቅደላ አምባምስል Alula Pankhurst

በጎርጎረሳዉያኑ 2017 ከዚህ ዓለም በሞት የተለዩት ታዋቂዉ የታሪክ ተመራማሪ ፕሮፌሰር ሪቻርድ ፓንክረስት፤ ጋር በመሆን የመቅደላ ቅርስ አስመላሽ ተቋም ‹‹አፍሮሜት››ን የመሰረቱት ፕሮፌሰር አንድርያስ እሸቴ የኢትዮጵያን ቅርሶችን የሚያሳየዉ ዓዉደ ርዕይ ለንደን ላይ መከፈቱ ኢትዮጵያን በማስተዋወቁ ረገድ በአወንታዊ መልኩ እንደሚያዩት ለቢቢሲ በሰጡት ቃለ ምልልስ ገልፀዋል። ቀደም ሲል የባህልና የቱሪዝም ቢሮ በሰጠዉ መረጃ መንግሥት ከሙዚየሙ ጋር ያደረገው ምንም ዓይነት ውይይት፣ ድርድር፣ ሐሳብ ልውውጥ የለም፡ ብሎ ነበር ። የታሪክና ቅርስ ከፍተኛ ተመራማሪዉ አቶ ኃይለመለኮት አግዘዉ እንደሚሉት በርካታ የኢትዮጵያ ቅርሶች በተለያየ መንገድ ከኢትዮጵያ ወጥተዋል።

Äthiopien Mekedela  Alula Pankhurst
መቅደላምስል Alula Pankhurst

ለንደን የሚገኘዉ የቪክቶሪያና አልበርት ሙዚየም ቅርሶቹን በዉሰት ለረጅም ጊዜ እሰጣለሁ ማለቱን ተከትሎ አዲስ አበባ የሚገኘዉ የ ባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር እንደማያውቀው ማስታወቁ ይታወሳል። የለንደኑ ሙዚየም ይህን መናገሩ እጁ ያስገባቸዉን የኢትዮጵያ ድንቅ ታሪካዊ ቅርሶች ለአንድ ዓመት ለተመልካች ክፍት ማድረጉን ተከትሎ ነው፡፡ በለንደን የሚገኘዉን ሙዚየም  በተለያዩ ጊዜያት የጎበኙት በለንደን የኢትዮጵያ ቅርፅ ማበልጸግያ ማኅበር ሊቀመንበር አቶ አለባቸዉ ደሳለኝ ይህ ነዉ የማይባል የተለያዩ ቅርሶችን እንዳዩ ተናግረዋል ።

በተባባሪ ፕሮፊስርነት በአዲስ አበባ ዩንቨርስቲ ለ 16 ዓመታት ያገለገሉትና በአሁኑ ወቅት ከኦክስፎርድ ዩንቨርስቲ ጋር በትብብር በወጣቶች ጉዳይ ላይ በሚሰራ ጥናት ላይ የኢትዮጵያ ተጠሪ ሆነዉ የበጥናቱ እየተሳተፉ የሚገኙት የታዋቂዉ የታሪክ ተመራማሪ የሪቻርድ ፓንክረስት ልጅ አሉላ ፓንክረስት እንደሚሉት በቅድምያ የቪክቶርያ አልበርት ሙዚየም ዳይሬክተር ይህንን ሃሳብ ያቀረበበትን ጉዳይ መግለጽ የሚያስፈልግ ይመስለኛል።  

ቅርሶቹን በዉሰት የሚለዉ ሃሳብ ለንደን እንጊሊዝ ከሚገኘዉ ሙዚየም ዳይሬክተር የመጣ ነዉ እንጂ ፤ የኢትዮጵያ መንግሥት ጠይቆ አይደለም ያሉት አቶ አሉላ ፓንክረስት እንዲያም ሆኖ የኢትዮጵያ መንግሥት የልዑል አለማየሁን ቅሪተ አፅም ጨምሮ ቅርሶች እንዲመለሱ  የኢትዮጵያ ሚሊኒየም ሲከበር የዝያን ጊዜዉ ፕሬዚደንት ግርማ ወልደጊዮርጊስ ጠይቀዉ እንደነበር አስታዉሰዋል።  አሉላ ፓንክረስት በአሁኑ ወቅት በለንደን ከተማ ቪክቶርያና አልበርት ቤተ-መዘክር የሚገኙት የኢትዮጵያ ንጉሳዉያን ቁሳቁሶች በ 12 ዝሆኖች እና ከ 200 በሚበልጡ የጋማ ከብቶች መጓጓዛቸዉን ጨምረዉ ተናግረዋል። በሙዚየሙ የሚገኙ ወደ 11 የሚሆኑት ታቦታት ለተመልካችን ጨርሶ እንዳይቀርቡም ታግደዋል ብለዋል።

Äthiopien Mekedela
ምስል Alula Pankhurst

በእንጊሊዝ ዉስጥ በርካታ የኢትዮጵያ ታሪካዊ ቅርስ በግለሰብ እጅ እንደሚገኝ በለንደን የኢትዮጵያ ቅርፅ ማበልጸግያ ማኅበር ሊቀመንበር አቶ አለባቸዉ ደሳለኝ ተናግረዋል ። እንደ አቶ አሉላ እስካሁን ከአስራ አምስት የሚሆኑ ቅርሶች ወደ ኢትዮጵያ እንደተመለሱ ገልፀዋል። ይህም ብለዋል የዜዎቹ የጦር ሰራዎቶች የልጅ ልጆች ቅድም አያቶቻቸዉ ትክክል እንዳልሰሩ እዉቅና መስቸጠታቸዉን የሚያሳይ ነዉ። በቅርቡ የጀነራል ናፒርልጅም አሉ አሉላ በመቀጠል አንድ ሃብልና አንድ ብራና መልሰዋል።

Äthiopien Mekedela  Alula Pankhurst
ምስል Alula Pankhurst

ኢትዮጵያ በብሪታንያ ወታደሮች የዛሬ 150 ዓመት የተዘረፉ ጥንታዊ ቅርሶች እና ለንደን ከተማ ዉስጥ የሚገኘዉን የአፄ ቴዎድሮስ ልጅ የልዑል አለማየሁ ቅሪተ አፅም እንዲመለስላት መጠየቅዋን የጀርመን የዜና አገልግሎት በዚሁ በያዝነዉ ሳምንት ዘግቦአል። የብሪታንያ ጦር ኢትዮጵያን በተለይም  ወርሮ መቅደላ ላይ የያኔዉ የኢትዮጵያ ንጉስ አፄ ቴዎድሮስ እራሳቸዉን የሰዉበት 150ኛ ዓመት በያዝነዉ ወር ይከበራል።በወረራዉ ወቅት የብሪታንያ ጦር  የንጉሳዉያን አልባሳት፤ የአንገት ሃብል፤ አክሊል ፤ ጥንታዊ የብራና ፅሑፎች እና ሌሎች  ቅርሶች እንዲመለሱ ዘርፏል።የኢትዮጵያ የባሕል እና ቱሪዚም ሚኒስትር ወይዘሮ ኂሩት ወልደማርያም ለጀርመኑ ዜና አገልግሎት በሰጡት መግለጫ፤-«የተዘረፉት የኢትዮጵያ ጥንታዊ ቅርሶች እንዲመለሱልን ለብሪታንያ  ደብዳቤ ልከናል፤ መልሱን በመጠባበቅ ላይ ነን፤ ቅርሶቹን በእጃችን ለማስገባት በሕግም ሆነ በዲፕሎማሲዉን መንገድ እንጠቀማለን » ብለዋል።

 እነዚህን ጥንታዊና ታሪካዊ ቅርሶች ለማስመለስ ጥረት ከተጀመረ ከ10 ዓመት በልጦታል።የብሪታን ባለሥልጣናት ቅርሶቹን ለኢትዮጵያ ለማዋስ ማቀዳቸዉ ቁጣ ማስነሳቱም ተጠቅሶአል።በጦርነቱ በሕጻንነታቸዉ ተማርከዉ ብሪታንያ ዉስጥ በወጣትነታቸዉ የሞቱት የአፄ ቴዮድሮስ ልጅ ፤ የልዑል አለማየሁ ቅሪተ አካልንም ለማስመለስ ጥረት እየተደረገ መሆኑ ተመልክቶአል።     

በገንዘብ በቦታ ፤ በምዝገባ እንዲሁም በጥበቃዉ ረገድ ከኢትዮጵያ በዝርፍያ በስርቆት ከሃገር ዉጭ የሚገኙ ቅርሶቻችንን ለማስመለስ እኛስ ምን ያህል ተዘጋጅተናል? የታሪክና ቅርስ ከፍተኛ ተመራማሪዉ አቶ ኃይለመለኮት አግዘዉ መልስ አላቸዉ።የኢትዮጵያ ቅርፅ ማበልጸግያ ማኅበር ሊቀመንበር አቶ አለባቸዉ ደሳለኝም ሰፊ ትንታኔ ሰጥተዋል።

ሙሉዉን መሰናዶ የድምፅ ማድመጫ ማዕቀፉን በመጫን ይከታተሉ

አዜብ ታደሰ

ነጋሽ መሐመድ