1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የብሪታንያዉ ጠቅላይ ሚኒስትር እና ያልተጠበቀ መግለጫ

ሐሙስ፣ ግንቦት 15 2016

የብሪታንያው ጠቅላይ ሚኒስትር ሪሺ ሱናክ እጅግ ባልተጠበቀ ሁኔታ ትላንተ‍ ማምሻውን እንደ ጎርጎረሳዉያኑ አቆጣጠር ሐምሌ 4 የጠቅላላ ምርጫ የሚካሄድበት ቀን መሆኑን አሳውቀዋል። ይህ ውሳኔ አብዛኛውን የብሪታንያን ህዝብም ሆነ ፖለቲከኞችን ያስገረመ ሲሆን የገዥውን የራሳቸውን ወግ አጥባቂ ፓርቲ ሳይቀር አስደንቋል።

https://p.dw.com/p/4gDLO
ሪሺ ሱናክ ፤ የብሪታንያ ጠቅላይ ሚኒስትር
ሪሺ ሱናክ ፤ የብሪታንያ ጠቅላይ ሚኒስትር ምስል Hollie Adams/REUTERS

የብሪታንያዉ ጠቅላይ ሚኒስትር እና ያልተጠበቀ መግለጫ

የብሪታንያው ጠቅላይ ሚኒስትር ሪሺ ሱናክ እጅግ ባልተጠበቀ ሁኔታ ትላንተ‍ ማምሻውን እንደ ጎርጎረሳዉያኑ አቆጣጠር  ሐምሌ 4 የጠቅላላ ምርጫ የሚካሄድበት ቀን መሆኑን አሳውቀዋል ፣ ይህ ውሳኔ አብዛኛውን የብሪታንያን ህዝብም ሆነ ፖለቲከኞችን ያስገረመ ሲሆን የገዥውን የራሳቸውን ወግ አጥባቂ ፓርቲ ሳይቀር አስደንቋል። በተለይ ምርጫው የወግ አጥባቂው ፓርቲ ባለፈው ወር በደረሰበት መካከለኛ ምርጫ ሽንፈት ማግስት መሆኑ ብዙ አነጋጋሪ አድርጎታል ሪሺ ሱናክ ከ 10 ቁጥር ዳውኒንግ ስትሪት መኖሪያና ፅህፈት ቤታቸው መግቢያ በር ላይ ለተሰበሰቡት ጋዜጠኞች እና ለመላው የብሪታንያ ህዝብ ባደረጉት ንግግር ሀምሌ 4 የምርጫ ቀን እንዲሆን መወሰናቸውን አስታውቀዋል።

“አሁን ለብሪታንያ የወደፊት እጣዋን የምትወስንበት ወቅትነው ምርጫው አንድና አንድ ነው ፣ወይ የጀመርነውን የዕድገት መንገድ ማስቀጠል ወይ ደግሞ ወደኋላ ተመልሰን የኢኮኖሚ አዘቅት ውስጥ በመግባት አገራችንን ወደኋላ መጎተት ይህ መንታ መንገድ እና አለመተማመንን የምናስቀርበት ቀን ወስነናል ይህንኑ በመተመለከተ ዛሬ ረፋዱ ላይ ንጉስ ቻርልስን ፓርላማውን እንዲያፈርሱ አቅርቤ ተስማምተዋል በተጨማሪም

ሀምሌ 4 የምርጫ ቀን አእንዲሆን ተወስኗል” የተቃዋሚው ሌበር ፓርቲ መሪ ሰር ኪየር ስታንመር ለደጋፊዎቻቸው ባደረጉት ንግግር

“ዛሬማምሻውን ጠቅላየሚኒስትሩ የጠቅላላ ምርጫ ቀን ሀምሌ 4 መሆኑን ወስነው ተናግረዋል ይህ ለብሪታንያ ሕዝብ ለውጥ ለማምጣትና አገራችንን ከውድቀት የሚታደግ ምርጫ ነው ዕድላችሁን ተጠቅማችሁ የሌበር ፓርቲ ላለፉት አራት አመታት በትጋት የሰራውን የለውጥ አመራርና ብሪታንያን ካለችበት ውድቀት ለማውጣት በምርጫው እንዲያሸንፍ በተባበረ ሀይል እንድንሰራ ያስፈልጋል”።

መኮንን ሚካኤል

አዜብ ታደሰ

ማንተጋፍቶት ስለሺ