1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የብልፅና እና የሲአን ቅንጀት

ረቡዕ፣ መጋቢት 15 2013

ገዢው የብልፅና ፓርቲና ተቃዋሚው የሲዳማ አርነት ንቅናቄ / ሲአን / በመጪው አገራዊ ምርጫ በጋራ ለመወዳደር ያስችለናል ያሉትን ቅንጅት መመስረታቸውን አስታወቁ።

https://p.dw.com/p/3r3pb
Äthiopien Koalition aus Prosperity Party (PP) und Sidama Liberation Movement (SLM)
ምስል Shewangzaw Wegayehu/DW

ገዢው የብልፅግና ፓርቲና ተቃዋሚው የሲዳማ አርነት ንቅናቄ / ሲአን / በመጪው አገራዊ ምርጫ በጋራ ለመወዳደር ያስችለናል ያሉትን ቅንጅት መመስረታቸውን አስታወቁ።

የፓርቲዎቹ አመራሮች ዛሬ ረፋድ ላይ በሀዋሳ በጋራ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ አንዳሉት የፊታችን ግንቦት ሊካሄድ በታቀደው ምርጫ በጥምረት ለመወዳደር ከሚያስችላቸው ስምምነት ላይ መድረሳቸውን ገልጸዋል።

ሁለቱ ድርጅቶች ላለፉት ሰባት ወራቶች በቅንጅት ለመስራት በሚያግቧቧቸው ጉዳዮች ላይ ሲወያዩ መቆየታቸውንና  በአሁወቅትም በአብዛኞቹ ነጥቦች ላይ በቅንጅት ለመስራት የሚያስችላቸውን ስምምነት መፈራረማቸውን የፓርቲዎቹ አመራሮች ተናግረዋል።

ቅንጅቱ ሌሎች ተፎካካሪ ፓርቲዎችን ለማዳካም ነው ትባላላችሁ ? በቅንጅት ተወዳድራችሁ ብታሸንፉ የክልላዊ መንግስት አወቃቀራችሁ ምን መልክ ይኖረዋል ? በሚል ከጋዜጣኞች ለቀረቡላቸው ጥያቄዎችም አመራሮቹ ምላሽ ሰጥተዋል።

 ሸዋንግዛዉ ወጋየሁ

አዜብ ታደሰ

ነጋሽ መሐመድ