1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የብልጽግና ፓርቲ መግለጫ እና አንድምታው

ሰኞ፣ ግንቦት 23 2013

ፓርቲው ጫናውን ለመቋቋም ቀጣዩን ብሔራዊ ምርጫ ማካሄድ እና 2ተኛ ዙር የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብን የውሃ ሙሌት ማከናወን ወሳኝ ናቸው ብሏል። አንድ ተንታኝ አሜሪካ በቅርቡ በኢትዮጵያ ባለሥልጣናት ላይ የጣለችው የጉዞ እገዳ ማዕቀብ ሌላ ዓላማን ያነገበ በመሆኑ ፓርቲው በስብሰባው ጠቅለል ያሉ ጂኦፖለቲካዊ ጉዳዮችን መመልከቱ ተገቢ ነው ብለዋል፡፡

https://p.dw.com/p/3uEwm
Logo Prosperity Party Ethiopia

የብልጽግና ፓርቲ መግለጫ እና አንድምታው

ገዢው የብልጽግና ፓርቲ ባለፈው ሳምንት ማጠናቀቂያ በካሄደውው ስብሰባ ባሁን ወቅት ኢትዮጵያ ላይ ተጋረጡ ያለው ፈተኝ ጉዳዮች የውስጥ እና የውጭ ቢሆኑም፤ አስቸኳይ ምላሽ የሚሻው ግን ቃጣናው ላይ ያንዣበበው የኃያላን ፍላጎት መሆኑን አስገንዝቧል። ፓርቲው በመግለጫው ጫናውን ለመቋቋም ቀጣዩን ብሔራዊ ምርጫ ማካሄድ እና ሁለተኛ ዙር የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብን የውሃ ሙሌት ማከናወን ወሳኝ ናቸው ብሏልም። የፓርቲውን መግለጫ በአዎንታዊ መልክ ማየታቸውን ለዶይቼ ቬለ የገለጹት አንድ የፖለቲካ ተንታኝ አሜሪካ በቅርቡ በኢትዮጵያ ባለሥልጣናት ላይ የጣለችው የጉዞ እገዳ ማዕቀብ ቀላልና ሌላ ዓላማን ያነገበ በመሆኑ ፓርቲው በስብሰባው ጠቅለል ያሉ ጂኦፖለቲካዊ ጉዳዮችን መመልከቱ ተገቢ ነው ብለዋል፡፡ የኦሮሞ ፌዴራላዊ ኮንግሬስ ምክትል ሊቀመንበር አቶ ሙላቱ ገመቹ ግን ፓርቲው ካወጣው መግለጫ መረዳት የሚቻለው መንግሥት አሁንም ለድርድር ቅድሚያ አለመስጠቱን ነው ብለዋል፡፡

ስዩም ጌቱ 

ኂሩት መለሰ

አዜብ ታደሰ