1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የቤይሩት ፍንዳታ እና ኢትዮጵያዉያን 

ረቡዕ፣ ሐምሌ 29 2012

በቤይሩት በተከሰተው ፍንዳታ እስካሁን ሁለት ኢትዮጵያዊያን የከፋ አደጋ ሲደርስባቸው ሰባት ሰዎች መጠነኛ ጉዳት እንደገጠማቸው በዚያው የሚገኘው የኢትዮጵያ ቆንስል ለዶቼ ቬለ አስታወቀ።  የቤይሩት መንግሥት ዓለምአቀፉ ማኅበረሰብ ርዳታ እንዲያደርግለት ጥሪ አቅርቦአል።

https://p.dw.com/p/3gSlR
Libanon | Gewaltige Explosion in Beirut
ምስል Getty Images/AFP/STR

በአደጋዉ ኢትዮጵያዉያን ስለመኖራቸዉ እየተጣራ ነዉ


በቤይሩት በተከሰተው ፍንዳታ እስካሁን ሁለት ኢትዮጵያዊያን የከፋ አደጋ ሲደርስባቸው ሰባት ሰዎች መጠነኛ ጉዳት እንደገጠማቸው በዚያው የሚገኘው የኢትዮጵያ ቆንስል ለዶቼ ቬለ አስታወቀ። በየሆስፒታሉ እና የህክምና ተቋማት የተጎዱ ዜጎችን የማፈላለግ ሥራ እየተከናወነ መሆኑን የተናገሩት በቤይሩት የኢትዮጵያ ቆንስላ ጀኔራል ተመስገን ዑመር አሳሳቢ የነበረው በመጠለያ የሚገኙ ኢትዮጵያዊያን ጉዳይ ነበር ደኅንነታቸው የተረጋገጠ ነው ብለዋል። ሆኖም ብዙ ሰው ቆስሎ ሊሆን እንደሚችል ግምታቸው መሆኑንም ተናግረዋል። 
ሊባኖስ ቤይሩት ላይ ትናንት በደረሰው ከባድ ፍንዳታ ከ 100 በላይ ሰዎች መሞታቸዉ ከስፍራዉ የሚወጡ ዘገቦች እያመላከቱ ነዉ። የሟቾች ቁጥር ሊጨምር እንደሚችል ተነግሮአል። ከ 4000 በላይ ሰዎች ተጎድተዋል። ለፍንዳታው መባባስ ምክንያት የሆኑት ርችቶችና አሞኒየም ናይትሬት የተባለው ንጥረ ነገር ሳይሆን እንዳልቀረ የፍንዳታውን ይዞታ የተመለከቱ ባለሙያዎች መናገራቸውን ዘገባዎች ያመለክታሉ። ፍንዳታው የተከሰተበት ስፍራ ከፍተኛ ፍንዳታ ሊያስከትሉ የሚችሉ ነገሮች የተከማቹበት መሆኑን የሊባኖስ የሀገር ውስጥ ደህንነት ኃላፊ አባስ ኢብራሂም ተናግረዋል። የቤይሩት ከንቲባም ከተማዋ የጦርነት ቃጣና መስላለች ብለዋል። የሕይወት አድን ሠራተኞች በፍርስራሽ ውስጥ የተቀበሩ ሰዎችን ለማውጣት ጥረት የጀመሩት ማለዳ ላይ ነው።  


ሰለሞን ሙጬ 


አዜብ ታደሰ 
ነጋሽ መሐመድ