1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የቤኒ ሻንጉል መስተዳድር ተቃዋሚዎችን ሾመ

ማክሰኞ፣ ጥቅምት 16 2014

የቤኒ ሻንጉል ጉሙዝ ክልላዊ መንግስት ባለፈዉ ሳምንት የስድስት ተቃዋሚ ፓርቲ ባለስልጣናት ሾሞ ነበር።አባሎቻቸዉ ከተሾሙላቸዉ ፓርቲዎች የተወሰኑት ሹመቱን ተቀብለዉታል።

https://p.dw.com/p/42D4C
Äthiopien | Benishangul Liberation Movement
ምስል Negassa Dessalgen/DW

የቤኒሻንጉል ሕዝብ ነፃነት ንቅናቄ ሹመቱን «እንቢኝ» አለ

የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልላዊ መንግስት ተቃዋሚ ፓርቲ፣ የቤኒሻንጉል ሕዝብ ነፃነት ንቅናቃ (ቤሕነን) የክልሉ መንግስት በቅርቡ ለፓርቲዉ ባለስልጣናት የሰጠዉን ሹመት  እንደማይቀበል አስታወቀ።የቤኒ ሻንጉል ጉሙዝ ክልላዊ መንግስት ባለፈዉ ሳምንት የስድስት ተቃዋሚ ፓርቲ ባለስልጣናት ሾሞ ነበር።አባሎቻቸዉ ከተሾሙላቸዉ ፓርቲዎች የተወሰኑት ሹመቱን ተቀብለዉታል።የቤኒሻንጉል ሕዝብ ነፃነት ንቅናቄ (ቤሕነን) ሶስት ባለስልጣናቱ ተሾመዉ ነበር።ይሁንና ፓርቲዉ ሹሙቱን «ያልተመከረበት»ና «የማናዉቀዉ» በማለት ዉድቅ አድርጎታል።

ነጋሳ ደሳለኝ 

ነጋሽ መሐመድ

እሸቴ በቀለ