የባህርዳሩ የገና ገበያ
ሰኞ፣ ታኅሣሥ 29 2011ማስታወቂያ
በከተማዋ ለእርድ የቀረቡ እንስሳት ገበያ እንዲሁም በዓሉን ስናከብርም የክርስቶስን መወለድ እያሰብን ያለንን ለሌላቸው በማካፈል መሆን እንዳለበት በከተማዋ ነዋሪ የሆኑት መምህር ንጉሱ አይተነው ተናግረዋል። መምህር ንጉሱ አይተነው በባህር ዳር ከተማ ምስራቀ ፀሐይ አዲሱ ሚካኤል የሰበካ ጉባዔ ምምህር ናቸው፡፡ መምህር ንጉሡ አንደሚሉት፣ የክርስቶስ ልደት በዓለም ደረጃ መከበር የጀመረው በንጉስ ቆስጠንጢኖስ ዘመነመንግስት ነው፡፡ በኢትዮጵያ ደረጃ በዓሉ መከበር የጀመረው ከንጉስ ዘረዐአ ያዕቆብ ዘመነ መንግስት ጀምሮ በዋናነት በቤተ-ክርስቲያን ብቻ አንደነበር ጠቅሰው ቀስ በቀስ ወደ ህዝብ አንደሰፋም አስረድተዋል፡፡
ዓለምነው መኮንን
አዜብ ታደሰ
አርያም ተክሌ