1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የጉጂው ግጭት

ረቡዕ፣ ታኅሣሥ 3 2011

ጉዳት ደርሶብናል የሚሉ ወገኖች ከሰኞ እስከ ትንናት በዘለቀው ግጭት 4 ሰዎች ሞተዋል፤ የተፈናቀሉም አሉ ቢሉም፣ የከተማይቱ ምክትል ከንቲባ ግን የሞቱት ቁጥር ሁለት እንደሆነ ገልጸው የተፈናቀለ ግን የለም ሲሉ ለDW ተናግረዋል።

https://p.dw.com/p/39yBR
Karte Äthiopien Ethnien EN

የጉጂው ግጭት

በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ጉጂ ዞን ቡሌ ሆራ ከተማ ቀበሌ 03 በቡርጂና በጉጂ ጎሳዎች መካከል ሰሞኑን በተቀሰቀሰ ግጭት የሰዎች ህይወት እና ንብረት መጥፋቱን DW የያነጋገራቸው የአካባቢው ነዋሪዎች እና የከተማይቱ ምክትል ከንቲባ አስታወቁ። በግጭቱ ጉዳት ደርሶብናል የሚሉ ወገኖች ከሰኞ እስከ ትንናት በዘለቀው ግጭት 4 ሰዎች ሞተዋል፤ የተፈናቀሉም አሉ ቢሉም፣ የከተማይቱ ምክትል ከንቲባ ግን የሞቱት ቁጥር ሁለት እንደሆነ ገልጸው የተፈናቀለ ግን የለም ሲሉ ለDW ተናግረዋል። አካባቢውም አሁን መረጋጋቱን ነው የገለጹት። 
ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር
ኂሩት መለሰ
እሸቴ በቀለ