1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የበይነ መረቡ ምኅዳር ፈተና የመቋቋምያ አማራጮች

ረቡዕ፣ ታኅሣሥ 8 2012

ማንነትን ለመሰወር እና ከአደገኛ ስለላም እራስን ለመጠበቅ ደካማ የኔትወርክ አገልግሎት ባላቸው አገራት ቶርን መጠቀም አስቸጋሪ መሆኑ አያጠያይቅም።በአሁኑ ወቅት ግለሰቦችንና እንደ ዶይቼ ቨለ "DW"ያሉ ድርጅቶች የበይነ መረብ ቅድመ ምርመራን ለመከላከል በስፋት የሚጠቀሙባቸው የኦንየን ድር ጣቢያዎችን መድረስ የሚችሉ ልዩ የቶር አውታረ መረቦችም አሉ።

https://p.dw.com/p/3V2QK
Tor Logo
ምስል Creative Commons

የበይነ መረብ ምኅዳር ፈተና እና መፍትሄዎቹ

የበይነ መረብ ኢንተርኔት ተጠቃሚ በሚሆኑበት ወቅት እራስዎን ምን ያህል እየተከላከሉ እንደሆነ የመሰረታዊ ደህንነትዎ ጉዳይ ምን እንደሚመስል የትኛዎቹን መረጃዎችዎን በግል መያዝ እንደሚጠበቅብዎት በተጨማሪም ከማን መደበቅ እንደሚኖርብዎት ጭምር የተለያዩ ጥያቄዎችን በህሊናዎ ማሰላሰል እና ጥንቃቄ ማድረግ ጠቃሚ ነው:: በተለይም እንደ ፌስቡክ ያሉ የማህበራዊ ሚድያ መካነ ድሮችን ለመጠቀም በሚመዘገቡበት ወቅት የአይ ፒ አድራሻዎችም ከመመዝገቡም በላይ ትክክለኛ ስምዎን፣ ስልክ ቁጥርዎን፣ ፎቶግራፍዎን የኢሜይል አድራሻዎን እና የይለፍ ቃል የምስጢር ጥያቄዎችን  ጭምር የሚጠይቁበት ፖሊሲ ያላቸው በመሆኑ ደህንነትዎን ለመጠበቅ ከተገቢው በላይ መረጃዎችን ከመስጠት መቆጠብ አደጋን ለመቀነስ ይረዳል:: 

በበይነ መረብ -ኢንተርኔት አጠቃቀም ወቅት ለሌሎች የምንታየው እንዴት ነው?

DW Shift - Neue Regelungen zum Tracking
ምስል imago/Ikon Images

በመሰረቱ ሁሉም የኢንተርኔት ትራፊክ የአውታረ መረብ ተደራሽነት እስካለው ድረስ ከማንኛውም ሰው እይታ የተሰወረ አይደለም:: ልክ አንድ የሚላክ ፖስታ ለተቀባዩ በትክክል እንዲደርሰው የውጭ ክፍሉ በፖስታ ሰራተኞች በሚገባ መነበብ እንዳለበት ሁሉ ፤ የዲጂታል ቴክኖሎጂ ግንኙነቶችም በተገቢው መንገድ ከአንዱ ወገን ወደሌላው እንዲተላለፉ አገልግሎት ሰጭዎቹ ብዙውን ጊዜ መነሻና መድረሻቸውን መመልከት እንዲሁም ያሉበትን ስፍራ ማወቅ የሚያስፈልጋቸው ሁኔታ ይኖራል::

እንደ ቶር ያሉ የመስመር ላይ ግንኙነት አገልግሎቶችን የሚጠቀም ግለሰብም ሳንሱር፣ ጠለፋ እና የመረጃ ምስጢሮች ስርቆትን ለመቀነስ በግንኙነት ወቅት ምን ዓይነት መረጃ እና መልዕክት እንደሚያስተላልፍ፤ መረጃውን ማን እንደሚያገኘው በተለይም ዲበ ውሂብን ከሚሰበስቡ እና ከሚጠይቁ መንግስታት፣ ህጋዊ ድርጅቶች እና ቴሌኮምኒኬሽን ሌላ ሶስተኛ አካላት የተሳካ የመስመር ግንኙነት ለመፍጠር እንዲረዳቸው ዲበ ውሂብን ማግኘት መቻላቸው ብቻ ሳይሆን መረጃው ቢገለጥ የሚያስከትለው ውጤት እና እንዴት አገልግሎት ላይ እንደሚውል ተገቢ የግንዛቤ አድማስ ሊኖረው ይገባል::  ምንም እንኳ ማንም ሰው የማያየን ከኮምፒውተር ጀርባ የተሸሸግን ቢመስለንም እንኳ በበይነ መረብ አጠቃቀም ወቅት መረጃዎች የእኛን ማንነት ሊያሳዩ ወይም ሊያሳውቁ ይችላሉ::

በመጀመሪያ ደረጃ የኮምፒውተሩ የኢንተርኔት ፕሮቶኮል አድሬሱ IP Address አለ:: ይህም የመኖሪያ አድራሻችንን ስልካችንን እና በየትኛው የኢንተርኔት መስመር እንደምንጠቀም ዝርዝር መረጃዎችን የሚሰጥ ነው:: በአሁኑ ወቅት የኢንተርኔት ተጠቃሚዎች በኮምፒውተራቸው ውስጥ በሚገኝ መረጃ ወይም ዳታ አማካኝነት ማንነታቸውን ማወቅ የሚቻልበት ደረጃ ላይ ተደርሷል:: ለምሳሌ ልዩ ኔትወርክ የተገጠሙላቸው የኢንተርኔት መክፈቻ (ብራውዘር) ባህሪያት የኮምፒውተሩ ስክሪን ስፋት እና አጠቃላይ መተግበሪያ ሥርዓቱ የሚጠቀሙበት ቋንቋ እንዲሁም የሰዓቱ ሁኔታ ሁሉ መረጃ ሰጭ ነው:: የተጠቃሚዎች ትክክለኛ የቁልፍ ጣት አሻራም ቢሆን በኮምፒውተር የደህንነት መስክ ትልቅ ሚና የሚኖረው ሲሆን 98 በመቶ የሚሆነው ተጠቃሚ ያለ አይ ፒ አድራሻው እንኳ ማንነቱ በቀላሉ እንዲታወቅ የሚያደርግ ነው::

Symbolbild Chinas große Firewall
ምስል picture-alliance/dpa

መንግስት የሚያግዳቸውን የተወሰኑ ድረ ገፆች እንዴት መድረስ /መከታተል/ ይቻላል? ስለ ማንነትን መሰወሪያ መረቦች

የኢንተርኔት ተጠቃሚዎች የተወሰኑ ድረ ገጾችን እንዳይመለከቱ ወይም አገልግሎቶችን በኢንተርኔት እንዳያገኙ የሚከለክሉ ሶፍትዌሮችን የሚጭኑ የመረጃ እና ሃሳብን በነጻነት የመግለፅ መብት የሚያፍኑ አያሌ ጨቋኝ መንግስታት እንዳሉ ይታወቃል:: አንዳንዶቹ ክልከላዎች በድረ ገፁ ኢንተርኔት ፕሮቶኮል ማለትም አይፒ አድራሻ ላይ ትኩረትን የሚያደርጉ ሲሆን ፤ ቀሪዎቹ ደግሞ የድረ ገጹን የኢንተርኔት መጠሪያ ወይም የዶሜን ስም በእገዳ መዝገብ ውስጥ በማስገባት የሚከናወኑ ናቸው። ከአሁን ቀደም በኢንተርኔት ላይ ወይም በታገዱ ድረ ገፆች ላይ የሚደረጉ ዕገዳዎችን ለማለፍ የሚያስችል ማንነትን እና ሳንሱርን የሚከላከል በታገደው ኮምፒውተርና በአገልግሎቱ መካከል ሆነው እንደ አገናኝ ድልድይ ጥቅም የሚሰጡ አገልግሎቶች ተግባራዊ ሆነው ቆይተዋል::

ብዙውን ጊዜ የበይነ-መረብ ትራፊክን የሚያስተላልፉትም ቀላል የአይ ፒ አድራሻዎች ብቻ ነበሩ። በአሁኑ ወቅት ግን መንግስታት የማይፈልጓቸውንና የሚጠራጠሯቸውን ስምአልባ ስውር መረቦች /proxy anonymity networks/ ማገድ ችለዋል:: በእርግጥም በአሁኑ ወቅት መንግሥታት ልዩ ልዩ ድርጅቶች የመረጃ እና ደህንነት መስሪያቤቶች፣ የትምህርት ተቋማት እና የቴሌኮሚዩኒኬሽን አገልግሎት ሰጭ ካምፓኒዎች የበይነ መረብ-ኢንተርኔት ተጠቃሚዎች የተለያዩ ድህረ ገጾችን እና የኢንተርኔት አገልግሎቶችን እንዳይጠቀሙ የሚያግዱ ሶፍትዌሮችን ስራ ላይ ያውላሉ:: ይህ ዓይነቱን የሆነ አካል የሚፈፅመው የግለሰቦችን የኢንተርኔት ግንኙነት እንዲሁም አይ ፒ አድሬስ የመቆጣጠር አልያም ድህረ ገጾችን የማገድ፤ በሌላ አገላለፅ የመስመር ላይ ሳንሱር ወይም የኢንተርኔት እገዳን ለማለፍ ደግሞ ልዩ ልዩ ዘዴዎችን መጠቀም ይቻላል::

Symbolbild Virtual Private Network VPN
ምስል picture alliance / dpa

ይኸውም ድርዎ የሚጠቀምበትን መስመር በመቀየር ማንነትን ምስጢራዊ አድርገው የሚይዙ መሳሪያዎችን መጠቀም ፣የታገደ ድህረ ገፅን ለማየት ተኪ እና የተመሰጠሩ ድህረ ገጾችን መጎብኘት፣ ምናባዊ የግል ኔትዎርክ /ቪፒኤን/ መጠቀም አልያም ማንነትን ለመደበቅ የሚረዳውን ቶር ብራውዘር መጠቀም አማራጮች ይሆናሉ:: ድረ ገጾችን ለማየት የሚጠቀሙት ፕሮግራም ፋየርፎክስ፣ ሳፋሪ፣ ኢንተርኔት ኤክስፕሎረርእና ክሮም ሁሉም የድር መዳሰሻ ናቸው::  የኢንተርኔት ግንኙነታችን እገዳዎቹን እንዲያልፍ የሚያደርገው አገልግሎት ደግሞ ተኪ ወይም በእንግሊዘኛው ፕሮክሲ በመባል የሚጠራው ነው::

ከአንድ አውታረ መረብ ወደ ሌላው መረጃዎች ያለስጋት እንዲዘዋወሩ የሚያስችል/የሚፈቅድ የግንኙነት ፕሮቶኮል እንዴት መመስረት ይቻላል?

Symbolbild - VPN
ምስል Colourbox/Tashatuvango

ምናባዊ የግል አውታረመረቦች ወይም(ቪፒኤን) በመጠኑ የተወሳሰቡ ናቸው ፡፡ ምናባዊ የግል ኔትዎርክ ወይም የ VPN አገልግሎት በሁለት ወይም የተለያዩ ወገኖች መካከል በኮምፒውተር የሚደረገውን የበይነ መረብ የውሂብ ልውውጥ አመስጥሮ የሚልክ ነው:: አገልግሎቱ በተገቢው መንገድ ኮምፒውተር ላይ ከተዋቀረ የተለያዩ ድህረ ገጾችን ለመጎብኘት ለኢሜል እና ፈጣን የመልዕክት አገልግሎት በተጨማሪም አይ ፒን ተጠቅሞ ለሚካሄድ የድምፅ ግንኙነት እና ለሌሎችም የኢንተርኔት አገልግሎቶች አያሌ ጠቀሜታ አለው:: ያም ቢሆን  VPN ትራፊክዎ በሌላ ሶስተኛ ወገን እንዳይሰለል ቢከላከልም አንዳንድ መንግስታት እና ተቋማት የግንኙነትዎን ዝርዝር ማግኘት የሚችሉበት እድልም ስላላቸው የጥቅሙን ያህል ጉዳትም እንደሚያስከትል ሊታወቅ ይገባዋል::

ቶር ምንድነው?

ሌላው የተጠቃሚዎችን መረጃ እና ደህንነት መጠበቂያ ሶፍትዌር ፕሮግራም ቶር ነው:: ቶር ማለት በድር ላይ የበይነ መረብ-ኢንተርኔት ተጠቃሚው ማንነት እንዳይታወቅ ለማድረግ የተሰራ ክፍት ምንጭ ሶፍት ዌር ነው:: በመሰረቱ የዲጂታል ማህበረሰብ የሚጠቀምባቸው አብዛኛዎቹ ሶፍት ዌሮች ክፍት ምንጭ እንዲሆኑ አንዳንድ የመስኩ ባለሙያዎች ይመክራሉ:: ይህም የሆነው እነዚህ ሶፍትዌሮች እንዴት እንደሚሰሩ ግልፅ በመሆኑ በሶፍትዌሩ ላይ ያሉ የደህንነት ወይም የጥንቃቄ ስጋቶችን ሌሎችም እንዲመረምሩት እና እንዲያሻሽሉት የሚጋብዝ በመሆኑ ነው:: ቶር ማሰሻ በቶር አኖኒሚት ኔትዎርክ የበላይነት የተሰራ የድር ማሰሻ ነው:: "ቶር ድር" የኢንተርኔት ተጠቃሚዎችን አሰሳ ሰብሮ ስለሚገባ ማንኛውንም ብሔራዊ የመንግስት እና የደህንነት ተቋማት እቀባን እንዲሁም የመስመር ላይ ሳንሱርን በቀላሉ ማለፍ ያስችላል:: ማንነትን ለመሰወር እና ከአደገኛ ስለላም እራስን ለመጠበቅ ቢረዳም እጅግ ዘገምተኛ እና ለአጠቃቀምም ትንሽ ከበድ ስለሚል ደካማ የኔትወርክ አገልግሎት ባላቸው አገራት ቶርን መጠቀም አስቸጋሪ መሆኑ አያጠያይቅም:: በአሁኑ ወቅት ግለሰቦችን እና እንደ ዶይቼ ቨለ "DW" ያሉ ድርጅቶች የበይነ መረብ ቅድመ ምርመራን ለመከላከል በስፋት የሚጠቀሙባቸው የኦንየን ድር ጣቢያዎችን መድረስ የሚችሉ ልዩ የቶር አውታረ መረቦችም አሉ:: ሆኖም ማንነትን መደበቅ ወይም መሰወር በተወሰነ ደረጃ የተከለከለ በመሆኑ አንዳንድ ሰዎች የቶር አውታረ መረብን ከመጠቀም እየተቆጡቡ መተዋል:: ቶር ሳንሱርን ለማስቅረት እና ከደንበኛ ትሪፊኮችን የሚቀበሉና ወደ ተጠቃሚው በቀላሉ የሚያጓጉዙ "ፕላጌብል ትራንስፖርትስ" የተሰኙ የረቀቁ ሶፍትዌሮችንም ጥቅም ላይ አውሏል:: 

Zensurumgehung
ምስል DW
Deutschland Anonym surfen | Tor-Browser
ምስል picture-alliance/dpa/A. Warnecke

በመስመር አገልግሎት የሚተላለፉ መልዕክቶች ከሚፈልጉት ተቀባይ ሰው ሌላ በሌላ አካል እንዳይነበብ በአሁኑ ጊዜ ምስጠራን ተግባራዊ ለማድረግ የሚያስችል ብቃት ያላቸው ኮምፒውተሮች አገልግሎት መስጠት ጀምረዋል:: የዲጂታል ማመስጠሪያ ቴክኖሎጂ ከጥቃቅን ምስጢራዊ መልዕክቶች ውጭ ለሌሎችም ተግባራት ማለትም የአንድ መልዕክት ጸሐፊን ማንነት ለማረጋገጥ ወይም ድርን በቶር ብራውዘር በምስጢር ማሰስ እስከማስቻልም ተደርሷል። ከዚህ ሌላ የበይነ መረብን የደህንነት ስጋትን ለመቀነስ እና የውሂብ ግላዊነትን መብት መጠበቅ የሚቻልባቸውን ስልቶች የቀየሱ ድህረ ገጾችን ለማየት የሚረዱ የግል ፕሮግራሞች አገልግሎት ላይ ውለዋል:: ውሂብ መረጃ ሰነዶችን፣ ስዕሎችን፣ ቁልፎችን፣ ፕሮግራሞችን፣ መልዕክቶችን እና ሌሎች ዲጂታል መረጃዎችን ወይም ፋይሎችን ሊያካትት ይችላል።

እነዚህ የበይነመረብ መፈለጊያ ፕሮግራሞች ተጠቃሚዎች ያለ እክል ስራቸውን እንዲያከናውኑ በ አይ ፒ ላይ በሚደረግ የድምፅ ግንኙነት ይኸውም ማንኛውም ኢንተርኔትን በመጠቀም የድምጽ ግንኙነት ለማድረግ የሚያገለግለው የቴክኖሎጂ አገልግሎት ደህንነቱ እንዲረጋገጥ የግል ማስታወቂያዎችም እንዳያውኩ አስፈላጊውን ጥረት ሁሉ የሚያከናውኑ ሲሆኑ የግል የመረጃ ስርዓቱም በመረጃ ቋቶች በመረጃ ቴክኖሎጂዎች ውስጥ እና በቴክኒካዊ አኳኋን የተካተቱ የግል መረጃ ስብስቦችን (ሂደቱን) መቆጣጠርን ያረጋግጣሉ:: የፋየርፎክስ እና ተዛማጅ የድር አሳሽ መክፈቻ ወይም ማሰሻ (ብራውዘሮችም)  ኩኪዎችን፣ ትራከሮችን ወይም እንደ ጃቫ ያሉ ስክሪፕቶችን የሚያግዱትን ለመከላከል ተጨማሪ የአድ-ኦንስ መተግበሪያዎችን ይጠቀማሉ::

Social Media-Nutzung in Afrika
ምስል AFP/Getty Images/I. Sanogo

በመሰረቱ ኩኪዎች ድረ ገጾች የድር መዳሰሻችንን እንዲያውቁ የሚያደርጉ የድር ቴክኖሎጂ መሆናቸው ይታወቃል። በተጨማሪም የድር ጉብኝታችንን እና የማንነታችንን መገለጫ እንዲሰበስቡም ስለሚያስችሉ ፤ ድረ ገጾች እኛን እንዲያውቁ እና የት እንደምንሄድ ፣ ምን አይነት መሣሪያን እንደምንጠቀም በተጨማሪም ምን ዓይነት ዝንባሌ እንዳለን ሁሉ ሊያውቁ ይችላሉ። የበይነ መረቡ ምህዳር የገጠመውን ውስብስብ ፈተና እና ስጋት ለመቋቋም የተለያዩ ግለሰቦች እና ድርጅቶች እንደ ክሮም እና ፋየርፎክስ ያሉ የድረ ገፆች ማሰሻዎችን በአማራጭነት የተኩትን ዱክዱክ ጎ እና ስታርት ፔጅን የመሳሰሉ ማሰሻዎችን በስፋት ሲጠቀሙም ይስተዋላል:: በቻይና የተጠናከረ እገዳ እና የበይነመረብ ሳንሱር እንደደረሰበት በመግለፅ የሚቃወመው ዶይቼ ቨለም "DW" ሳይፈን/PSiphon/ የሚባለው አፕ በአሁኑ ወቅት ፕሮግራሞቹን በቀላሉ ለማውረድና ለተለያዩ አፕሊኬሽኖች ከፍተና እገዛ እንደሚያደርግለትም አስታውቋል።ይህ አፕ አምባገነን መንግሥታት የሚፈጽሙትን የድረ ገጾች እገዳና ሳንሱር የመቋቋም ጠንካራ አቅም እንዳለው ጠቁሞ አድማጮች መረጃዎችን በቀጥታ በኢሜል አድራሻው dw-w@psiphon3.com ሊያገኙ እንደሚችሉ መልዕክቱን በዚህ አጋጣሚ ያስተላልፋል።

እንዳልካቸው ፈቃደ 

ኂሩት መለሰ