1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የሠላም ጉባኤ

ዓርብ፣ መጋቢት 13 2011

በጉባኤዉ ላይ ከበኒ ሻንጉል ጉሙዝ የባንባሲ እና የማኦ ኮሞ፣ከኦሮሚያ ደግሞ የቤጊና የቆንዳለ ወረዳዎች ነዋሪዎች ፣የኃይማኖት መሪዎችና የሐገር ሽማግሌዎች ባጠቃላይ ከ1500 የሚበልጡ ጉባኤተኞች ተካፍለዋል።

https://p.dw.com/p/3FVc4
Äthiopien, Friedenskonferenz zwischen Oromia und Benishangul Gumuz
ምስል DW/N. Dessalegn

የሠላም ጉባኤ

 

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልልና በኦሮሚያ አዋሳኝ አካባቢዎች ተከስቶ በነበረዉ ግጭት የተፈጠረዉን መቃቃር ለማስወገድ ያለመ የሠላም ጉባኤ ሰሞኑን ተደርጓል።በጉባኤዉ ላይ ከበኒ ሻንጉል ጉሙዝ የባንባሲ እና የማኦ ኮሞ፣ከኦሮሚያ ደግሞ የቤጊና የቆንዳለ ወረዳዎች ነዋሪዎች ፣የኃይማኖት መሪዎችና የሐገር ሽማግሌዎች ባጠቃላይ ከ1500 የሚበልጡ ጉባኤተኞች ተካፍለዋል።ጉባኤተኞቹ እንዳሉት በተደጋጋሚ በተከሰቱ ግጭቶች የተፈናቀሉትን ወደየቀያቸዉ ለመመለስ፣የተጎዱ ሰዎችን ለመርዳት፣ የጠፋ ሐብትን ለማስመለስና ወንጀለኞችን ለሕግ ለማቅረብ ይጥራሉ።በበኒ ሻንጉልን ከኦሮሚያ ጋር በሚያዋስኑ ድንበሮች ካለፈዉ ክረምት ጀምሮ በተደረጉ ግጭቶች በመቶ የሚቆጠር ሰዉ ተገድሏል፣ በብዙ ሺሕ የሚቆጠር ተፈናቅሏል።ግጭቱ እንዳይደገም ይረዳሉ የተባሉ ጉባኤና ዉይይቶች በተደጋጋሚ እየተደረጉ ነዉ።

ነጋሳ ደሳለኝ 

ነጋሽ መሐመድ

አዜብ ታደሰ