1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የበኒ ሻንጉል ተፈናቃዮች ብዛትና ርዳታ

ዓርብ፣ ነሐሴ 14 2013

የቤኒሻንል ጉሙዝ ክልል የአደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽ ኃላፊ አቶ ታረቀኝ ታሲሳ  በክልሉ ከ2010 ዓ.ም አንስቶ የተፈናቀሉ ዜጎች ቁጥር ከ4 መቶ ሺ በላይ ሲሆን ከእነዚህም መካከል የመተከል ዞን ከፍተኛውን ቁጥር ይይዛል፡፡ ለተፈናቀሉ ዜጎችም ከጉባ እና ወምበራ ወረዳዎች በስተቀር በመደበኛነት ድጋፎች እየተደረጉ እንደሆነም ሀላፊ አስረድተዋል

https://p.dw.com/p/3zHaR
Äthiopien | Asosa City
ምስል Negassa Dessalgen/DW

«ከበኒ ሻንጉል ክልል የተፈናቀሉት ከግማሽ ሚሊዮን ይበልጣሉ» ተመድ

 

በበኒሻጉል ጉሙዝ ክልል በሰው ሰራሽ እና በተፈጥሮ አደጋ ተፈናቅለው ለነበሩ  ከ417 ሺህ 800 ለሚበልጡ ዜጎች ሰብአዊ ድጋፍ  እሰጠ መሆኑን የክልሉ የአደጋ ስጋት እና ስራ አመራር ኮሚሽን አስታወቀ፡፡ የኮሚሽኑ ኃላፊ አቶ ታረቀኝ ታሲሳ ለዶቸ ቬለ  እንደተናገሩት  ተፈናቃዮች ወደ ቀድሞ ቀያአቸው ተመልሰው እስኪቋቋሙ ድረስ ኮሚሽኑ መርዳቱን ይቀጥላል።የተባበሩት መንግስታት የሰብአዊ ጉዳዩች ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ባለፈው ሰኞ ባወጣው ዘገባ ግን  በኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የተፈናቀሉት ሰዎች ቁጥር 540ሺ እንደሚደርስ ገልጦ ነበር።ዓለም አቀፉ ድርጅት እንደዘገበዉ በደቡብ ክልል፣በሶማሌ፣በአማራ፣በወለጋ እና አፋር ክልል የተፈናቀሉ ዜጎች ቁጥር ባጠቃላይ ከአራት ሚሊዩን በላይ ነዉ።በበኒ ሻጉል ጉሙዝ በካማሺ፣በመተከል እና አሶሳ ዞን ውስጥ በተፈጥሮ አደጋ እና ሰው ሰራሽ አደጋዎች  እንዲሁም ስማቸው በውል ያልታወቁ የታጣቂዎች ጥቃት በደረሰው ጉዳቶች ከዚህ ቀደም ዜጎች መፈናቀላቸውን የተባበሩት መንግስታት የሰብአዊ  ጉዳዩች ማስተባበሪያ ጽህፈት ቤት መረጃ ያመለክታል፡፡ የተባበሩት መንግስታት የሰብአዊ ጉዳዩች ማስተባበሪያ ጽህፈት ቤት የኢትዩጵያ ቅርንጫፍ ባለፈው ሰኞ ባወጣው ዘገባ መሰረት ከአራት ሚሊዩን በላይ የተፈናቀሉ ዜጎች በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች ይገኛሉ፡፡ በቤኒሻንል  ጉሙዝ ክልል  የአደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን መረጃ መሰረት ደግሞ በክልሉ ከዚህ ቀደም በነበሩት ግጭቶች ምክንያት 360ሺ በላይ ዜጎች በጊዜያዊ መጠለያ ጣቢያው ውስጥ ይገኛሉ፡፡

የቤኒሻንል ጉሙዝ ክልል የአደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽ ኃላፊ አቶ ታረቀኝ ታሲሳ  በክልሉ ከ2010 ዓ.ም አንስቶ የተፈናቀሉ ዜጎች ቁጥር ከ4 መቶ ሺ በላይ ሲሆን ከእነዚህም መካከል የመተከል ዞን ከፍተኛውን ቁጥር ይይዛል፡፡ ለተፈናቀሉ ዜጎችም ከጉባ እና ወምበራ ወረዳዎች በስተቀር በመደበኛነት ድጋፎች እየተደረጉ እንደሆነም ሀላፊ አስረድተዋል፡፡ በመንግስት እና ግብረ ሰናይ ድርጅቶች በሚሰጡት ድጋፎች በየወሩ ለአንድ በተሰብ በየወሩ 15 ኪ.ሎ እህል ለተፈናቀሉ ዜጎች እንደሚደርስም ጠቁመዋል፡፡

ከሶስት ወራት በፊት ከካማሺ ዞን ሰዳል ወረዳ  የተፈናቀሉ ዜጎች በባምባሲ ወረዳ በተዘጋጀው ጊዜያዊ መጠለያ ጣቢያ  ውስጥ ይገኛሉ፡፡  ከሴዳል ወረዳ በሚያዚያ ወር ተፈናቅለው በአሶሳ የሚገኘው አቶ ዩሰፍ ታደሰ  የዕለት ደራሽ እርዳዎች በምግብ ዋስትና በኩል የሚቀርቡ ሲሆን ለአንድ በተሰብ  በቂ አለመሆኑን ገልጸዋል፡፡ ጊዜያዊ መጠለያ ጣቢያ ያልገቡ ተፈናቃዩችም እርዳታ እየደረሳቸው እንዳሆነም ጠቁመዋል፡፡

የተባበሩት መንግስታት የሰብአዊ ጉዳዩች ማስተባበሪያ ጽህፈት ቤት በኢትዮጵያ የተለያየ ክልሎች በነበሩት የጸጥታ ችግሮች ተፈናቅለው ያሉት ዜጎች ሰብአዊ እርዳ እንደሚያስፈልጋቸው አመልክቷል፡፡ በሪፖርቱ መሰረት በቤኒሻንል 538000፣ በደቡብ 1.4 ሚሊየን፣ በወለጋ 51000 እና በሌሎች ክልሎች በርካቶች ተፈናቅለው እንዳሉ አብራርተዋል፡፡ በቤኒሻጉል ጉሙዝ ክልል ከተፈናቀሉ ዜጎች በተጨማሪ ከ90 በላይ ትምህርት ቤቶች ላይ ጉዳት መድረሱንና እና 41 ትምህርት ቤቶች ደግሞ ሙሉ በሙሉ መውደማቸውን ዘገባው አመልክቷል፡፡ 

ነጋሳ ደሳለኝ

ነጋሽ መሐመድ

አዜብ ታደሰ