1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

አንበጣ  በሰሜን ኢትዮጵያ ያደረሰው  ጥፋት

ሰኞ፣ ጥቅምት 2 2013

በተለይም በትግራይ፣ አማራ እና አፋር ክልል አዋሳኝ አካባቢዎች በነበረን ቅኝት በርካታ አርሶአደሮች ማሳ ላይ የነበረ የማሽላና ጤፍ ምርት በአንዳንድ አካባቢዎች ሙሉ በሙሉ በሌላ አካባቢ ደግሞ በከፊል መውደሙን ዘጋቢያችን ሚሊዮን ኃይለ ሥላሴ ተመልክቷል።

https://p.dw.com/p/3jp7o
Äthiopien | Heuschreckenplage an der Grenze zu Tigray und Amhara
ምስል Million H. Silase/DW

አንበጣ  በሰሜን ኢትዮጵያ ያደረሰው  ጥፋት

መነሻውን የመንና የቀይ ባሕር ዳርቻዎችን ያደረገ የበረሃ አንበጣ መንጋ፣ በኢትዮጵያ የተለያዩ አካባቢዎች እየተሰራጨና ሰብል እያወደመ ይገኛል። በተለይም በትግራይ፣ አማራ እና አፋር ክልል አዋሳኝ አካባቢዎች  በርካታ አርሶአደሮች ማሳ ላይ የነበረ የማሽላና ጤፍ ምርት በአንዳንድ አካባቢዎች ሙሉ በሙሉ በሌላ አካባቢ ደግሞ በከፊል መውደሙን ዘጋቢያችን ሚሊዮን ኃይለ ሥላሴ ተመልክቷል። ሚሊዮን እንደዘገበው አርሶ አደሮቹ የአንበጣ መንጋውን ድምፅ በመፍጠር እና የተለያዩ ባህላዊ ዘዴዎች ተጠቅመው ለመከላከል ጥረት ቢያደርጉም ከአቅማቸው በላይ እንደሆነባቸው ይናገራሉ። 

ሚሊዮን ኃይለ ሥላሴ
ኂሩት መለሰ
ሸዋዬ ለገሠ