1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የቀጠለው ጎሳ ተኮር ግጭት

እሑድ፣ መስከረም 20 2011

በልዩ ልዩ የኢትዮጵያ ክፍሎች ጎሳን መሠረት ያደረጉ ግጭቶች ጎላ ብለው መታየት ከጀመሩ ከሁለት አስርት ዓመታት በላይ ተቆጠረ። በተለይ ደግሞ ከአስር ዓመት ወዲህ ተባብሰው ታይተዋል። በግጭቶቹ የሰዎች ክቡር ሕይወት እንደዋዛ ተቀጥፏል፣ ዜጎችም ለብዙ ዓመታት ተደላድለው ኑሯቸውን ካደረጁበት አካባቢ ሲፈናቅልም ታይቷል።

https://p.dw.com/p/35fuf
Äthiopien Proteste in Addis Abeba
ምስል picture-alliance/AP Photo/M. Ayene

ጎሳ ተኮር ግጭት ፖለቲካዊም ሆነ ባህላዊ መፍትሄ የለው ይሆን?

ለግጭት ቁርቁሱ መነሻ ለአንዳንዶች ቋንቋን መሠረት ያደረገው የፌደራል አስተዳደር ክፍፍል ነው። ሌሎች ደግሞ ወቅት ያመጣው እና ሊያከስመው የሚችል ይሉታል። ለመባባስ መካረሩ የተበላሸ የፖለቲካ ጨዋታው ቢወቀስም፤ ይህንን ሊያርቅ የሚችል ሥር የሰደደ የሽምግልናው ባህላዊ ወግ መዳከም ማነጋገሩ አልቀረም። ዶይቼ ቬለ የቀጠለው ጎሳ ተኮር ግጭት እና መፈናቀል ፖለቲካዊም ሆነ ባህላዊ መፍትሄ የለው ይሆን? በማለት ያጠያይቃል። ሙሉ ቅንብሩን ከድምፅ ዘገባው ያድምጡ።

ሸዋዬ ለገሠ

ማንተጋፍቶት ስለሺ