1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የቀድሞው ብአዴን ኢሕአዴግ ሲፈርስ እጁን በማስገባቱ የህወሓት ሊቀ-መንበር ወቀሱ

ቅዳሜ፣ ታኅሣሥ 25 2012

ኢሕአዴግን የመሰረተው የቀድሞው ብአዴን/አዴፓ በመፍረሱ ሒደት እጁን በማስገባቱ ደብረ ጺዮን ገብረሚካኤል ወቀሱ። የትግራይ ክልል ምክትል ርዕ-መስተዳድር ወቀሳ የተደመጠው ህወሓት በታሪኩ ለመጀመሪያ ጊዜ እያካሔደ በሚገኘው አስቸኳይ ጉባኤ ላይ ባደረጉት ንግግር ነው።

https://p.dw.com/p/3ViVP
Äthiopien Tagung der Volksbefreiungsfront von Tigray
ምስል DW/M. Haileselassie

ህወሓት አስቸኳይ ጉባኤውን ጀምሯል

ህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) በታሪኩ ለመጀመሪያ ግዜ አስቸኳይ ጉባኤ እያካሄደ ነው፡፡ ህወሓት በአስቸኳይ ጉባኤው በኢህአዴግ ውህደት ዙርያ የመጨረሻ ውሳኔ ላይ ይደርሳል፣ ቀጣይ ጉዞው አመላካች አቅጣጫ ያስቀምጣል ተብሏል፡፡ በህወሓት አስቸኳይ ጉባኤ መክፈቻ ስነ ስርዓት ላይ ንግግር ያሰሙት የፓርቲው ሊቀ መንበር ዶክተር ደብረፅዮን ገብረሚካኤል ኢህአዴግን በማፍረስ ብአዴን/አዴፓ ተብሎ ይታወቅ የነበረው በቅርቡ የከሰመው ፓርቲ  ከሰዋል፡፡

ሚሊዮን ኃይለስላሴ

እሸቴ በቀለ