1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የሻሸመኔው ቀውስ እና የተከሰተው ጥፋት

ሰኞ፣ ሰኔ 29 2012

የአርቲስት ሃጫሉ ሁንዴሳን ሞት ተከትሎ በሻሸመኔ ከተማ ተከስቶ በነበረው ነውጥ የሁለት ሰዎች ህይወት አልፎ በከተማዋ ከፍተኛ የንብረት ውድመት መድረሱን የከተማዋ አስተዳደር አስታወቀ። በከተማዋ ተፈጥሮ በነበረው ችግር ከሞት እና ንብረት ውድመት ባሻገር 242 ሰዎች ከቤት ንብረታቸው መፈናቀላቸውን የከተማ ከንቲባ አቶ ተማም ሁሴን ተናግረዋል።

https://p.dw.com/p/3es9q
Äthiopien Unruhen in Shashemene
ምስል Privat

«መንግስት ተመጣጣኝ እርምጃ አለመውሰዱ ጥፋቱን አባብሶታል»

የአርቲስት ሃጫሉ ሁንዴሳን ሞት ተከትሎ በሻሸመኔ ከተማ ተከስቶ በነበረው ነውጥ የሁለት ሰዎች ህይወት አልፎ በከተማዋ ከፍተኛ የንብረት ውድመት መድረሱን የከተማዋ አስተዳደር አስታወቀ። በከተማዋ ተፈጥሮ በነበረው ችግር ከሞት እና ንብረት ውድመት ባሻገር 242 ሰዎች ከቤት ንብረታቸው መፈናቀላቸውን የከተማ ከንቲባ አቶ ተማም ሁሴን በተለይ ለዶይቸ ቬለ ተናግረዋል። በተፈጠረው  ረብሻ ከተማዋ ትታወቅባቸው የነበሩ የንግድ እና ቱሪዙም መዳረሻ ሆቴሎች እና የንግድ ሕንጻዎች መውደማቸውንም ተናግረዋል።በሻሸመኔ ከተማ በተፈጠረው እና ከፍተኛ ጉዳት አስከትሎ ያለፈውን ይኸንኑ ችጉሩ የከፋ ጉዳት ከመድረሱ በፊት መንግስት ተመጣጣኝ እርምጃ አለመውሰዱ ውድመቱ እንዲፈጠር አድርጓል ብለዋል።በሻሸመኔ ከተማ ተከስቶ  በነበረው በዚሁ ነውጥ ተሳታፊ የነበሩትን በቁጥጥር ስር ለማዋል ጥረት እየተደረገ መሆኑን የተናገሩት አቶ ተማም እስካሁን 98 ሰዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን አስታውቀዋል።

ታምራት ዲንሳ

አዜብ ታደሰ