1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የሺንፋ ዉጊያ፣የአማራና የቅማንት ዉዝግብ

ሐሙስ፣ ነሐሴ 27 2013

የምዕራብ ጎንደር ዞን አስተዳዳሪ «የቅማንት ፅንፈኛ» ያሏቸዉ ኃይላት ከሕዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ (ሕወሓት) ታጣቂዎች ጋር አብረዉ ሺንፋ የተባለችዉን ከተማ ለመያዝ ትናንት ያደረጉት ሙከራ «ከሽፏል» ብለዋል

https://p.dw.com/p/3zpgm
Äthiopien | Region um Quara und Shinfa
ምስል Alemnew Mekonnen/DW

የአማራ ክልል ባለስልጣናትና የቅማንት ዉዝግብ

የአማራ ክልል መንግስት እና  የቅማንት ዴሞክራሲያዊ  ፓርቲ (ቅዴፓ) ባለስልጣናት ምዕራብ ጎንደር ዉስጥ በተደረገ ዉጊያ ሰበብ እንዳዲስ እየተወዛገቡ ነዉ።የአማራ ክልል በተለይም የምዕራብ ጎንደር ዞን አስተዳዳሪ «የቅማንት ፅንፈኛ» ያሏቸዉ ኃይላት ከሕዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ (ሕወሓት) ታጣቂዎች ጋር አብረዉ ሺንፋ የተባለችዉን ከተማ ለመያዝ ትናንት ያደረጉት ሙከራ «ከሽፏል» ብለዋል።ቅዴፓ ግን የቅማንት ኃይላት በትናንቱ ዉጊያ ተሳትፈዋል መባሉን ሐሰት ብሎታል።አንድ የፓርቲዉ ከፍተኛ ባለስልጣን እንዳሉት አዲሱ ወቀሳ ከዚሕ ቀደም የአማራ ክልል ባለስልጣናት በቅማንት የፖለቲካ ኃይሎች ላይ ከሚሰነዝሩት የተለየ ዓይደለም።ትናንት ዉጊያ ተደረገበት የተባለዉ አካባቢ ከኢትዮ-ሱዳን ድንበር በቅርብ ርቀት ላይ ይገኛል።

ዓለምነዉ መኮንን 

ነጋሽ መሐመድ

ኂሩት መለስ