የስፖርት ጥንቅር 19.11.2013
ሰኞ፣ ሐምሌ 19 2013ማስታወቂያ
በጉጉት የተጠበቀው በጃፓን የሚካሄደው የኦሊምፒክ ስፖርታዊ ውድድሮች በርካታ አትሌቶች ለረዥም ጊዜ የተዘጋጁበት እንደመሆኑ ብዙዎች ከወዲሁ ሜዳሊያዎችን ለየሀገራቸው ማስቆጠር ጀምረዋል። በቀዳሚነትም ቻይና ዩናይትድ ስቴትስ እና ራሷ አስተናጋጇ ሀገር ጃፓን በርካታ ሜዳሊያዎችን በማግኘት ከፊት ተሰልፈዋል። በዘንድሮው ኦሎምፒክ 11 ሺህ ገደማ አትሌቶች ይሳተፋሉ። ኢትዮጵያ በዚህ ኦሎምፒክ ከዚህ በፊት ባልተሳተፈችባቸው የስፖርት ዘርፎች ትሳተፋለች። ወቅቱ የኮሮና ተሐዋሲ ስጋት ያጠላበት ቢሆንም ከዚህ ባልተናነሰ ሞቃቱ የአየር ጠባይ ለተሳታፊ አትሌቶች ፈታኝ መሆኑ ተነግሯል። በሌላ በኩል ታዋቂው የጀርመኑ ባየር ሙኒክ የእግር ኳስ አጥቂ ሮበርት ሌቫንዶቭስኪ የጀርመን ዓመቱ ምርጥ ተጫዋች ተብሏል። ሌሎችም ዝርዝር ስፖርታዊ መረጃዎችን ለማድመጥ የድምጽ ማዕቀፉን ይጫኑ።
ሃይማኖት ጥሩነህ
ሸዋዬ ለገሠ