1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የስፖርት እና ባሕል ድግስ በለንደን

ረቡዕ፣ ሐምሌ 10 2011

ዘጠነኛው የስፖርት እና ባሕል ድግስ ባሳለፍነው ሳምንት መጨረሻ በለንደን ተካሂዷል። በስፍራው ተገኝታ ዝግጅቱን የተከታተለችው የለንደኗ ዘጋቢያችን ሃና ደምሴ እንደምትለው ለሁለት ቀናት የተካሄደው የማኅበረሰቡ በአል ለሕጻናት መዝናኛ አስቦበት ነበር።

https://p.dw.com/p/3MD9e
Aussichtsplattformen dieser Welt Tulip Tower London  (picture-alliance/Dbox for Foster + Partners)
ምስል picture-alliance/Dbox for Foster + Partners

ለዘጠነኛ ጊዜ የተዘጋጀ ነበር

ቅዳሜ እና እሁድ ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያ በስፍራው ተገኝተው የተሳተፉበት ይህ የስፖርት እና የባሕል ድግስ የተለያዩ የባሕል ምግቦች፤ ጌጣ ጌጦች፣ አልባሳት መቅረባቸውን፤ ግብረ ሰናይ ድርጅቶችም በስፍራው ተገኝተው ለታዳሚው አገልግሎታቸውን መስጠታቸውንም በላከችው ዘገባ አመልክታለች።   ዘጋቢያችን  ያነጋገረቻቸው በስፍራው የገኙ ታዳሚዎች ስለዝግጅቱ አስተያየታቸውን ሰጥተዋል። እንዲህ ባለው ዝግጅትም ለመጀመሪያ ጊዜ በለንደን የኢትዮጵያ ኤምባሲ መገኘቱም ተሰምቷል።

ሃና ደምሴ

ሸዋዬ ለገሠ

አዜብ ታደሰ