1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የስድስት ሃገራት አምባሳደሮች የመቀሌ ጉብኝት 

ሰኞ፣ መስከረም 26 2012

መቀመጫቸው አዲስአበባ ያደረጉ የስድስት ሃገራት አምባሳደሮች የኢንቨስትመንት ዕድሎችና የቱሪዝም ሀብት ለመመልከት ያለመ ጉብኝት በትግራይ አካሄዱ፡፡ አምባሳደሮቹ ከኢንዱስትሪዎች በተጨማሪ ጥንታዊው አልነጃሺ መስጊድ ተመልክተዋል፣ ከትግራይ ክልል ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣት ጋር ተወያይተዋል፡፡

https://p.dw.com/p/3QqJ9
Botschafter von China, Turkey, India und Iran
ምስል DW/M.Hailessilasie

የኢንቨስትመንት ዕድሎችና የቱሪዝም ሀብት ለመመልከት ያለመ ጉብኝት

መቀመጫቸው አዲስአበባ ያደረጉ የስድስት ሃገራት አምባሳደሮች የኢንቨስትመንት ዕድሎችና የቱሪዝም ሀብት ለመመልከት ያለመ ጉብኝት በትግራይ አካሄዱ፡፡ በክልሉ መንግስትና ኢትዮ ነጃሺ በተባለ ድርጅት አስተባባሪነት በተካሄደው ይህንኑ ግብኝት የቱርክ፣ ካዛኪስታን፣ ባንግላዲሽ፣ ስሪላንካ፣ ፓኪስታንና ኢንዶኔዥያ አምባሳደሮች ተገኝተውበታል፡፡ አምባሳደሮቹ ከኢንዱስትሪዎች በተጨማሪ ጥንታዊው አልነጃሺ መስጊድ ተመልክተዋል፣ ከትግራይ ክልል ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣት ጋር ተወያይተዋል፡፡ ይኽ በእንዲህ እንዳለ በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሳደር ማይክል ሬነር ዛሬ ከስዓት በመቐለ የስራ ጉብኝት አድርገዋል፡፡ አምባሳደር ማይክል ሬነር በመቐለ ቆይታቸው ከመቐለ ዩኒቨርሲቲ ምሁራንና የህወሓት አመራሮች ጋር በኢትዮ ኤርትራ ሰላም ጉዳይ ዙርያ እንደተወያዩ አንድ የስብሰባው ተሳታፊ ነግረውናል፡፡  በተጨማሪም በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሳደር ማይክል ሬነር ከቆይታቸው ከትግራይ ንግድና ዘርፍ ማሕበራት አመራሮች ጋርም ተወያይተዋል ተብሏል፡፡


ሚሊዮን ኃይለሥላሴ
አዜብ ታደሰ 
ማንተጋፍቶት ስለሺ