1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል
እምነትአፍሪቃ

የስቅለት በዓል አከባበር በአዲስ አበባ

ዓርብ፣ ሚያዝያ 14 2014

በመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች እና በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በልዩ ሐይማኖታዊ ስርዓት የሚከበረው የኢየሱስ ክርስቶስ የስቅለት በዓል ዛሬ በደማቅ ሐይማኖታዊ ስርዓት ተከብሮ ዋለ። የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ፓትሪያርክ ብፁእ ወቅዱስ አቡነ ማቲያስ እለቱን በማስመልከት መልእክት አስተላልፈዋል።

https://p.dw.com/p/4AJN2
Äthiopien Addis Abeba | Holy Trinity Cathedral Market
ምስል Seyoum Getu/DW

በደማቅ ሐይማኖታዊ ስርዓት ተከብሯል

በመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች እና በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በልዩ ሐይማኖታዊ ስርዓት የሚከበረው የኢየሱስ ክርስቶስ የስቅለት በዓል ዛሬ ተከብሮ ዋለ። የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ፓትሪያርክ ብፁእ ወቅዱስ አቡነ ማቲያስ እለቱን በማስመልከት ባስተላለፉት መልእክት ሕዝበ ክርስቲያኑ ከጾሙ በረከት እንዲያገኝ ጥላቻን በመተው ከኢየሱስ ክርስቶስ ፍቅርና ይቅር ባይነትን መውረስ ይገባል ብለዋል። በርካታ የእምነቱ ተከታይ ምእመንም እለቱን በስግደትና በጸሎት አስታውሰውት ውለዋል። ለኢትዮጵያ ሰላምም ጸልየዋል። ዘጋቢያችን  ከአዲስ አበባ መንበረ ፓትርያርክ ቅድስተ ቅዱሳን ማሪያም ገዳም እና በመንበረ ጸባኦት ቅድስት ሥላሴ ቤተ ክርስትያን የተከናወነውን ስርዓት ተከታትሎት ነበር።

Äthiopien Addis Abeba | Holy Trinity Cathedral Market
ምስል Seyoum Getu/DW

በመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች ዘንድ የሚከበረው የኢየሱስ ክርስቶስ ስቅለት በዓል በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን እንደ ወትሮው በደማቅ ሐይማኖታዊ ስርዓት ነው ተከብሮ ውሏል። የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ፓትሪያርክ ብፁእ ወቅዱስ አቡነ ማቲያስ በመንበረ ፓትርያርክ ቅድስተ ቅዱሳን ማሪያም ገዳም ተገኝተው ነው ስርዓቱን ያከናወኑት። እለቱን በማስመልከትም መልእክት አስተላልፈዋል። ቅዱስ ፓትሪያርኩ የእንኳን አደረሳችሁ መልካም ምኞታቸውንም አስተላልፈዋል።

የእምነቱ ተከታይ ምእመንም ስለ እለቱ እና ተግባራቱ አስተያየታቸውን አካፍለውናል። በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን እና አጠቃላይ እንደ አገር የሚደርሱ ፈተና ያሏቸውን በማለፍ የተረጋጋች አገር እንድትኖርም መንግስትም ሕዝቡም የድርሻቸውን ቢወጡ ብለዋልም በአስተያየታቸው።

ሥዩም ጌቱ

ማንተጋፍቶት ስለሺ

እሸቴ በቀለ