1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የሳህል አካባቢ ሃገራት ድጋፍ ጉባኤ

ሐሙስ፣ ታኅሣሥ 5 2010

በአፍሪቃ ሳህል አካባቢ እየተባባሰ የመጣዉን የሽብር እንቅስቃሴ፤ የተንሰራፋዉን ሕገ ወጥ የሰዎች አሸጋጋሪዎች እና የአደንዛዥ ዕፅ አዘዋዋሪዎች መረብ ለመበጣጠስ ያለመ ድጋፍ ተሰባሰበ።

https://p.dw.com/p/2pOF5
Gipfeltreffen in Bamako Mali
ምስል Reuters/L. Gnago

የፀረሽብር እንቅስቃሴዉን ለማጠናከር ያለመ ነዉ

ትናንት ከፓሪስ አቅራቢያ የቡድን አምስት ሃገራትን ለመደገፍ የተካሄደዉ ጉባኤ በኢኮኖሚ ልማት እና ፀጥታ ላይ ተመርኩዞ የተመሠረተዉን ቡድን ተልዕኮዉ ለማፋጠን በገንዘብ እና በቴክኒክ ለመደገፍ ተስማምቷል።  ኒዠር፣ ሞሪታንያ፣ ቻድ፣ ማሊ እና ቡርኪናፋሶ ለተካተቱበት ቡድን ተልዕኮ ሳዉድ አረቢያ 100 ሚሊየን ዶላር እንዲሁም የተባበረዉ አረብ ኤሜሬቶች 30 ሚሊየን ዶላር ለመስጠት ቃል ገብተዋል። የአዉሮጳ ኅብረት እና ዩናይትድ ስቴትስም በገንዘብ እና ወታደራዊ ቁሳቁስ ለመደገፍ መዘጋጀታቸዉን አስታዉቀዋል። በስብሰባዉ ላይ የጀርመኗ መራሂተ መንግሥት አንጌላ ሜርክል፤ የፈረንሳዩ ፕሬዝደንት ኢማኑኤል ማክሮ እና ሌሎች 15 የሃገራት መሪዎች እና ተወካዮች እንዲሁም የአፍሪቃ ኅብረት እና የአዉሮጳ ኅብረት ተገኝተዋል። ከፓሪስ ሃይማኖት ጥሩነህ ዝርዝር ዘገባ አላት።

ሃይማኖት ጥሩነህ

ሸዋዬ ለገሠ

አርያም ተክሌ