የሲዳማ ክልል አንደኛ ዓመት
ማክሰኞ፣ ሰኔ 29 2013ማስታወቂያ
ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መስተዳድር ተነጥሎ ባለፈዉ ዓመት የራሱን ክልላዊ መስተዳድር የመሰረተዉ የሲዳማ ብሔር ክልላዊ መስተዳድር አንደኛ ዓመት የምሥረታ በዓሉን ዛሬ አክብሮ ዉሏል።የቀድሞዉ የሲዳማ ዞን በክልል ደረጃ የተዋቀረዉ የአካባቢዉ ተወላጆች ለተከታታይ ዓመታት ከታገሉና ከደም አፋሳሽ ግጭት በኋላ በተደረገ ሕዝበ ዉሳኔ ነዉ።የቀድሞዉ የሲዳማ ዞን የኢትዮጵያ 10ኛዉ ክልላዊ መስተዳድር ሆኖ ከተዋቀረ ካለፈዉ ዓመት ወዲሕ የሲዳማ ተወላጆች ያገኙት ወይም ያጡት ጥቅም ግን አሁንም እንዳነጋገረ ነዉ።
ሸዋንግዛዉ ወጋየሁ
ነጋሽ መሐመድ
እሸቴ በቀለ