1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የሱዳን ከፍተኛ ባለሥልጣን የኢትዮጵያ ጉብኝት

ሰኞ፣ ጥር 16 2014

የሕዝብ ቁጣ በአደባባይ እያመሳት የምትገኘው የሱዳን ሉዓላዊ ምክር ቤት ፕሬዝዳንት ጀነራል ሞሐመድ ሀምዳን ዳጋሎ ባለፉት ሁለት ቀናት ኢትዮጵያን ጎብኝተዋል። በለሥልጣኑ በሁለትዮሽ እና ቀጣናዊ የጋራ ጉዳዮች ሊመክሩ እንደሚችሉ ከመዘገቡ በቀር በቅልጽ የተነገረ ነገር የለም።

https://p.dw.com/p/4610U
Sudan General Abdel Fattah al-Burhan
ምስል Mahmoud Hjaj/AA/picture alliance

የሱዳን ሉዓላዊ ምክር ቤት ፕሬዝዳንት በኢትዮጵያ ምን ተወያዩ?

የሕዝብ ቁጣ በአደባባይ እያመሳት የምትገኘው የሱዳን ሉዓላዊ ምክር ቤት ፕሬዝዳንት ጀነራል ሞሐመድ ሀምዳን ዳጋሎ ባለፉት ሁለት ቀናት ኢትዮጵያን ጎብኝተዋል። በለሥልጣኑ በሁለትዮሽ እና ቀጣናዊ የጋራ ጉዳዮች ሊመክሩ እንደሚችሉ ከመዘገቡ በቀር በቅልጽ የተነገረ ነገር የለም።

በዚሁ ዙሪያ ዶይቼ ቬለ ያነጋገራቸው ሁለት የቀጣናዊና የፖለቲካ ተንታኞች እንደሚሉት ከሆነ ግን ዳጋሎ በዋናነት ሱዳን በወረራ በያዘችው የኢትዮጵያ መሬት፣ በአካባቢው ሰላምና መረጋጋት እንዲሰፍን ፣ እንዲሁም አገሪቱ በብርቱ የገጠማትን የውስጥ ችግር ለመፍታት ኢትዮጵያ ሁነኛ አገር መሆኗን ቆም ብለው ማጤን መጀመራቸውን መነሻ አድርገው ከኢትዮጵያ ባለስልጣናት ጋር ሊወያዩ እንደሚችሉ ገልፀዋል። ባለሙያዎቹ አክለው እንዳሉት የኢትዮጵያ ታላቁ የሕዳሴ ግድብ ኃይል የማመንጨት ጊዜ መቃረብም ጀነራሉ ለመምከር የመጡበት ሌላኛው ጉዳይ ሊሆን ይችላል።

አዜብ ታደሰ

እሸቴ በቀለ

እሸቴ በቀለ