የሰኔ 15 ተጠርጣሪዎች የችሎት ውሎ
ሰኞ፣ ሐምሌ 29 2011ማስታወቂያ
እንዲያም ሆኖ ሌሎች ምስክሮችን ቃል ለመቀበልም ሆነ ተጨማሪ ማስረጃዎችን ለማሰባሰብ ተጨማሪ የ14 ቀን የጊዜ ቀጠሮ ጠይቋል። የተጠርጣሪ ጠበቆች ባንፃሩ ደንበኞቻቸውን ለማጉላላት ነው በሚል በመቃወማቸው ፍርድ ቤቱ ግራ ቀኙን በማድመጥ የተጠየቀውን ተጨማሪ ጊዜ ውድቅ ማድረጉን ከባሕር ዳር ዘጋቢያችን ዓለምነው መኮንን በላከው ዜና አመልክቷል።
በተጠቀሰው ቀን ውስጥ አቃቢ ሕግ ክስ እንዲመሰረትና ታራሚዎችም ማረሚያ ቤት እንዲቆዩ ፍርድ ቤቱ ወስኗል። በሰኔ 15ቱ ጥቃት በአማራ ክልል ድርጊቱን ፈፅመዋል ተብለው የተጠረጠሩ 218 ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር ውለው ጉዳያቸው ሲጣራ ከቆየ በኋላ አብዛኛዎቹ መፈታታቸውን የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን አበረ አዳሙ ሰሞኑን ገልፀው ነበር፣ ሆኖም ድርጊቱ ውስብስብና የሚሳሳብ በመሆኑ ተጠርጣሪዎች አሁንም እየተያዙ እንደሆነ ከዶየቼ ቬለ ራዲዮ ጋር በነበራቸው ቆይታ አመልክተዋል። ሰኔ 15/2011 ጀኔራል አሳምነው ጽጌ መርተውታል በተባለውና የኢትዮጵ መንግስት መፈንቅለ መንግሥት ብሎ በጠራው ድርጊት የአማራ ክልል ርአስ መስተዳድር ነበሩት ዶ/ር አምባቸው መኮንንና ሌሎች ሁለት ከፍተኛ የክልሉ ባለስልታናት፣ ከቀናት በኋላ ደግሞ የድርጊቱ ጠንሳሽ ናቸው የተባሉት ብርጋደየር ጀኔራል አሳምነው ፅጌ መገደላቸው ይታወሳል።
ዓለምነው መኮንን
ሸዋዬ ለገሠ
ኂሩት መለሰ