የሰብዓዊ መብት ጥሰት መባባስ
ማክሰኞ፣ ጥቅምት 17 2013ማስታወቂያ
የኢትዮጵያ የሰብአዊ መብቶች ሕብረት፦ መንግሥት አፋኝ የሚባሉ ሕግጋት በማሻሻል ተቋማትን ለሰብአዊ መብት ጥሰት ከመጠቀም በመቆጠብ ረገድ መልካም ሥራዎችን ቢያከናውንም የመብት ጥሰት ግን አሳሳቢ ደረጃ መድረሱን አመለከተ። የአንዱ ብሔር አባል የሌላውን፣ የአንዱ ቡድን አባልም እንዲሁ የሌላው ላይ ጥቃት የሚፈጽምበት፤ ጥቃቶቹም ከተፈጸሙ በኋላ ወደሕግ ይወሰዳል ይባላል፤ አንዳንድ አመራሮችም ላይ ርምጃ ለመውሰድ እንቅስቃሴ ይደረጋል ሆኖም ይህ ተቋማዊ ተደርጎ መፍትሄ ካልመጣለት በቀር የታሰበውን ዓላማ ሊመታ እንዳልቻለ የሰብዓዊ መብቶች ሕብረት ዋና ሥራ አስፈጻሚ ለዶቼ ቬለ ገልጸዋል። ይኽ የመብት ጥሰት እና ጥቃት መሰረታዊ ችግር ኾኖ እንደሚታይም ተገልጧል። ሰለሞን ሙጬ ከአዲስ አበባ ቀጣዩን ዘገባ ልኮልናል።
ሰለሞን ሙጬ
ሸዋዬ ለገሠ
ማንተጋፍቶት ስለሺ