1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነትና የምዕራባውያን ጫና

ሐሙስ፣ ጥቅምት 4 2014

ምዕራባውያኑ መንግስታት በኢትዮጵያ ቀውስን ያስከተለውና በቀጠናው ስጋት ነው ባሉት በሰሜን ኢትዮጵያው ጦርነት ለማስቆም የተለያዩ አማራጮችን በማጤን ላይ መሆናቸውን እየገለጹ ነው፡፡

https://p.dw.com/p/41gak
Äthiopien Lalibela
ምስል Gabrielle Weise/Avalon/picture alliance

ማዕቀብ ሊያስከትል የሚችለው ተጽእኖ ቀላል አይደለም

ምዕራባውያኑ መንግስታት በኢትዮጵያ ቀውስን ያስከተለውና በቀጠናው ስጋት ነው ባሉት በሰሜን ኢትዮጵያው ጦርነት ለማስቆም የተለያዩ አማራጮችን በማጤን ላይ መሆናቸውን እየገለጹ ነው፡፡ ዶይቼ ቬለ ያነጋገራቸው የምጣኔ ሃብት እና የፖለቲካ ተንታኞች ኢትዮጵያ ላይ ባሁን ወቅት የሚጣል የትኛውም አይነት ማዕቀብ ሊያስከትል የሚችለው ተጽእኖ ቀላል ባለመሆኑ የሰሜን ኢትዮጵያውን ጦርነት ማሳጠር አለዚያም በሌላ አማራጭ መቋጨት የግድ ነው ሲሉ መክረዋል፡፡ ግብርና ላይ በትኩረት መስራት እና የኢትዮጵያን ኢኮኖሚ ከውጭ ገበያ የበዛ ጥገኝነት ማላቀቅና ከመርህ የራቀን የዲፕሎማሲ አቅጣጫ መከተል ሌላው አንገብጋቢ ነጥቦች ናቸው ብለዋል ብለሙያዎቹ፡፡

 

ስዩም ጌቱ

አዜብ ታደሰ

ኂሩት መለሰ