1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የሰሜን አሜሪካዉ ተቃዉሞ  

ማክሰኞ፣ ጥር 19 2012

«ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ የት አሉ?» ሲሉ የሚጠይቁ በሰሜን አሜሪካ ዋሽንግተን ዲሲ እና አካባቢዋ የሚኖሩ ኢትዮጵያዉያን የታገቱ የደምቢዶሎ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎችን ጉዳይ መንግሥት ለምን ዝም አለ ሲሉ ቁጣቸዉን አሰሙ።

https://p.dw.com/p/3WwH4
Bring Back our girls-Demonstration in DC Dembi Dollo Universität
ምስል DW/A. Belew

በሰሜን አሜሪካ ዋሽንግተን ዲሲ እና አካባቢዋ የሚኖሩ ኢትዮጵያዉያን የታገቱ የደምቢዶሎ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎችን ጉዳይ መንግሥት ለምን ዝም አለ ሲሉ ዛሬ የተቃዉሞ ሰልፍ እያካሄዱ ነዉ። ሰላማዊ ሰልፈኞቹ የታገቱት ተማሪዎች ይለቀቁ፤ መንግሥት ተማሪዎቹ ያሉበትን ሁኔታ ይንገረን፤ ዶ/ር ዐቢይ የት አሉ? ሲሉ ጠይቀዋል። ሰልፈኞቹ ይህን ቁጣቸዉን የገለፁት በዋሽንግተን በሚገኘዉ የኢትዮጵያ ኤንባሲ ቅፅር ጊቢ ፊት ነዉ። በአሁኑ ሰዓት በኢትዮጵያ የምናየዉ ሁኔታ በጣም አሳሳቢ ደረጃ ላይ እየደረሰ ነዉ ያሉት ዶቼ ቬለ ያነጋገራቸዉ የሰልፉ አስተባባሪ ጋዜጠኛ አበበ በለዉ፤ በአሁኑ ሰዓት ከ 24 በላይ የሚሆኑ የደንቢዶሎ ዩንቨርስቲ ተማሪዎች በአጋቾች ተይዘዉ ፤ የት እንደደረሱ ሳይታወቅ 52 ቀናት ሞልቶዋቸዋል ብለዋል። መንግሥት በዚህ ጉዳይ ላይ እያደረገ ያለዉ አንዳችም እንቅስቃሴ መኖሩን በይፋ ለማሳወቅ የተቸገረበት ጊዜ ነዉ፤ በአንድ ወቅት አቶ ንጉሡ ወጥተዉ ተለቀዋል ከማለት በዘለለ ከቤተሰቦቻቸዉ ማገናኘት ያልቻሉበት ሁኔታን ነዉ እያየን ያለዉ ሲሉም አክለዋል።» የዋሽንግተን ዲሲዉን የኢትዮጵያዉያን ተቃዉሞ በተመከተ የድምፅ ማድመጫዉን ማዕቀፉን በመጫን ይከታተሉ።    

አዜብ ታደሰ

እሸቴ በቀለ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ