1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የሰለሞን ድል

ዓርብ፣ ሐምሌ 23 2013

የ21 ዓመቱ ወጣት፣ ከዩጋንዳዊዉ የዓለም የ10 ሺሕ ሜትር ሻምፒዮን ከጆሽዋ ቼፕቴጊ እና ከሌለኛው ዩጋንዳዊ ዕውቅ አትሌት ጄኮብ ኪፒሊሞ ጠንካራ ፉክክር ቢገጥመውም ወርቁን አላስነካቸውም

https://p.dw.com/p/3yL4t
Japan Tokio | Olympische Spiele 2020 | Selemon Barega
ምስል Charlie Riedel/AP Photo/picture alliance

ቶኪዮ-ጃፓን በተያዘው የዓለም ኦሎፒምክ ውድድር በወንዶች የ10 ሺሕ ሜትር ሩጫ ኢትዮጵያዊው አትሌት ሰለሞን ባረጋ የወርቅ ሜዳይ አሸነፈ።የ21 ዓመቱ ወጣት፣ ከዩጋንዳዊዉ የዓለም የ10 ሺሕ ሜትር ሻምፒዮን ከጆሽዋ ቼፕቴጊ እና ከሌለኛው ዩጋንዳዊ ዕውቅ አትሌት ጄኮብ ኪፒሊሞ ጠንካራ ፉክክር ቢገጥመውም ወርቁን አላስነካቸውም። ሰለሞን ርቀቱን ያጠናቀቀው በ27 ደቂቃ፤ ከ43.22 ሴኮንድ ነው። ዩጋንዳውያኑ የብርና የነሐስ ተሸላሚ ሆነዋል። ሰሎሞን ከሁለት ዓመት በፊት በተደረገው የዓለም ሻምፖዮን በ5ሺሕ ሜትር የነሐስ አሸናፊ ነበር።ዛሬ ሳምንቱን በደፈነው የ2020 የዓለም ኦሎምፒክ ውድድር ቻይና በ18፣ አስተናጋጅዋ ጃፓን በ17፣ ዩናይትድ ስቴትስ በ14 የወርቅ ሜዳያዎች ካንደኛ እስከ ሦስተኛ ያለውን ሥፍራ ይዘዋል። ኢትዮጵያ ሰሎሞን ዛሬ ባስገኘላት ወርቅ 47ኛ ደረጃ ላይ ትገኛለች።

ነጋሽ መሐመድ

ሸዋዬ ለገሰ