1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የርሃብ አድማቸውን የገቱት ፖለቲከኞች የህክምና ሂደት

ሰኞ፣ የካቲት 29 2013

ለ40 ቀን ያህል በረሃብ አድማ ላይ ስለመቆየታቸው የተነገረውና በአሁኑ ወቅት በአንድ የግል ሆስፒታል በህክምና ላይ ያሉት ፖለቲከኛ ጃዋር መሃመድ፣ አቶ በቀለ ገርባ እና አቶ ሃምዛ አዳነ ትናንት የረሃብ አድማውን ለመግታት ከተስማሙ በኋላ አሁን ላይ ምግብ ለመጀመር በህክምና ሂደት ላይ መሆናቸውን ከጠበቆቻቸው አንዱ ለዶይቼ ቬለ ገለፁ፡፡ 

https://p.dw.com/p/3qMVK
Äthiopien Politiker Bekele Gerba
ምስል Addis Standard Magazine

የርሃብ አድማቸውን የገቱት ፖለቲከኞች የህክምና ሂደት

የርሃብ አድማቸውን የገቱት ፖለቲከኞች የህክምና ሂደት
ለ40 ቀን ያህል በረሃብ አድማ ላይ ስለመቆየታቸው የተነገረውና በአሁኑ ወቅት በአንድ የግል ሆስፒታል በህክምና ላይ ያሉት ፖለቲከኛ ጃዋር መሃመድ፣ አቶ በቀለ ገርባ እና አቶ ሃምዛ አዳነ ትናንት የረሃብ አድማውን ለመግታት ከተስማሙ በኋላ አሁን ላይ ምግብ ለመጀመር በህክምና ሂደት ላይ መሆናቸውን ከጠበቆቻቸው አንዱ ለዶይቼ ቬለ ገለፁ፡፡ ባለፈው ሳምንት በህክምና ማዕከሉ «ከቤተሰቦቻቸው የመገናኘትና በነጻነት ህክምናቸውን የመከታተል መብት ላይ ታካሚዎቹ ቅሬታ ነበራቸው» ያሉት ጠበቃ ከድር ቡሎ አሁን ላይ ሁሉም ነገር እልባት ማግኘቱን አብራርተዋል። የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) በበኩሉ የታካሚዎቹን ጉዳይ በቅርበት እየተከታተለ መሆኑን አሳውቋል፡፡

ስዩም ጌቱ

ልደት አበበ

አዜብ ታደሰ