1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የሩዋንዳ ዘር ጭፍጨፋ 25ኛ ዓመት መታሰቢያ

እሑድ፣ መጋቢት 29 2011

የጀርመኑ የዉጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሃይኮ ማስ በሩዋንዳ የዛሬ 25 ዓመት የተካሄደዉን የዘር ጭፍጨፋ አስመልክቶ እንደተናገሩት «ይህ ርዋንዳ ላይ ጥቁር ነጥብ ጥሎ ያለፈ ታሪክ፤ ለመጭዉ ትዉልድ ማስጠንቀቅያ ነዉ፤ ሊደገም የማይገባ ክስተት» ሲሊ ገልፀዉታል።

https://p.dw.com/p/3GQmM
Ruanda 25. Jahrestag Völkermord | Zeremonie in Kigali | Juncker & Ahmed & Michel
ምስል Reuters/B. Ratner

ሩዋንዳ  25 ዓመት የሆነዉና አንድ ሚሊዮን ገደማ የሚቆጠር ሕዝብ ያለቀበትን የዘር ጭፍጨፋ ዛሬ በይፋ አስባ ዋለች። መዲና ኪጋሊ ላይ በተካሄደዉ የዘር ጭፍጨፋ 25ኛ ዓመት መታሰቢያ ዝግጅት ላይ የአዉሮጳ ኅብረት ኮሚሽን ፕሬዚዳንት ዦንክሎድ ዩንከርን ጨምሮ የኢትዮጵያዉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ እንዲሁም በርካታ የዓለም መንግሥታት ተጠሪዎችና ተወካዮች ተገኝተዋል። ተጋባዥ እንግዶች እና የሩዋንዳ ፕሬዚዳንንት ፖል ካጋሜ ከ250 ሺህ በላይ የሚሆኑ የሩዋንዳ የዘር ጭፍጨፋ ሰለባዎች መካነ-መቃብር ላይ የአበባ ጉንጉን አኑረዋል። ሩዋንዳ በጀርመን እና በቤልጂየም ቅኝ ግዛት ስር ሳለች በጎርጎረሳዉያኑ 1994 ዓ.ም ብቻ  በሁቱ ጎሳ አባላት ለዘብተኛ የሚባሉ የሁቱ ጎሳ አባላትን ጨምሮ በርካታ የቱትሲ ጎሳ አባላት ተገድለዋል። የጀርመኑ የዉጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሃይኮ ማስ እንደተናገሩት ይህ ርዋንዳ ላይ ጥቁር ነጥብ ጥሎ ያለፈ ታሪክ « ለመጭዉ ትዉልድ ማስጠንቀቅያ ነዉ»  ሊደገም  የማይገባ  ክስተት » ሲሊ ገልፀዉታል። በመታሰብያ ሥነስርዓቱ ላይ ከባለቤታቸዉ ከቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታየቸዉ ጋር የተገኙት የኢትዮጵያዉ ጠቅላይ ሚ/ር ዐቢይ አሕመድ በሥነስርዓቱ ላይ ንግግር ማድረጋቸዉ ታዉቋል።    

አዜብ ታደሰ

እሸቴ በቀለ