1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የሥራ ዕድል ለበኒ ሻንጉል ወጣቶች

ዓርብ፣ ሐምሌ 30 2013

በተለያየ የትምህርት ዘርፍ ከከፍተኛ የትምሕርት ተቋማት የተመረቁ ወጣቶች በአንጻሩ ከ2 እና ከዛም በላይ ዓመት በተመረቁበት የትምህርት  ዘርፍ ስራ አለማግኘታቸውን ይገልጻሉ። ቁጥራቸዉ ትንሽ ቢሆንም በራሳቸው ተነሳሽነት ደግሞ በአሶሳ ከተማ በተለያዩ የስራ ዘርፍ የተሰማሩና ለውጥ ያመጡ ወጣቶችም ለሌሎች አርአያ የሚሆኑ ስራዎች ሰርተው ተስተውለዋል።

https://p.dw.com/p/3yfAQ
Young Graduates in  Benishangul Gumuz Complain of unemployment
ምስል Negassa Desalegn/DW

የሥራ ዕድል ለበኒ ሻንጉል ወጣቶች

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል በ2013 ዓ.ም በጀት ዓመት ከ20ሺ በላይ ለሚሆኑት ዜጎች ቋሚ እና ጊዜያዊ የስራ ዕድል መፍጠሩን የክልሉ መንግስት 12 መደበኛ ጉባኤውን ባካሄደበት ወቅት አስታውቋል፡፡  በክልሉ፣ ከተለያዩ የትምህርት ዘርፍ ከከፍተኛ የትምሕርት ተቋማት የተመረቁ ወጣቶች በአንጻሩ ከ2 እና ከዛም በላይ ዓመት  በተመረቁበት የትምህርት  ዘርፍ ስራ አለማግኘታቸውን ይገልጻሉ፡፡ በሌላ በኩል ቁጥራቸዉ ትንሽ ቢሆንም በራሳቸው ተነሳሽነት ደግሞ በአሶሳ ከተማ በበተለያዩ የስራ ዘርፍ የተሰማሩ እና  ለውጥ ያመጡ ወጣቶችም ለሌሎች አርአያ የሚሆኑ ስራዎች ሰርተው ተስተውለዋል።ከሶስት ዓመት በፊት ከኮሌጅ እንደተመረቀ የሚናገርው  ወጣት አዩብ  የአሶሳ ከተማ ነዋሪ ሲሆን በከተማው  የአሌክትሪክ ስራዎችን በመስራት ይታወቃል፡፡ ከዚህ ቀደም የኮቭድ 19ኝን ለመከላከያ በተሰሩ ስራዎችም ለመጀመሪያ ጊዜ በአሶሳ ከተማ ከእጅ ንክኪ ነጻ የየሆነ የእጅ መታጠቢያ ማሽን መስራቱን ገልጸዋል፡፡ 400 የሚደርሱ ከእጅ ንክኪ የጸዳ የእጅ መታጠቢያ ማሽኖችን ለተለያዩ ተቋማት ያቀረበ ሲሆን በአሁኑ ጊዜ ደግሞ የተለያዩ የብረታ ብረት ስራዎችን በመስራት ላይ ይገኛል፡፡አዩብ፣ በስራ ፈጠራ የተሰማሩ ወጣቶችን የማበረታታትና ድጋፍ የማድረግ ባህል በክልሉ መዳበር እንዳለበት ይላልም።

Young Graduates in  Benishangul Gumuz Complain of unemployment
ምስል Negassa Desalegn/DW

ወጣት ዩሐንስም የአሶሳ ከተማ ነዋሪ እና በ2011  በሲቪል ምህንድስና የተመረቀ ሲሆን በተመረቀበት ትምህርት እስካሁን አላገኘም።በክልሉ ባሉት የስራ ዘርፎች ለመሳተፍ በተለይም በስራ ዕድል ፈጠራ ኤጅንሲ በኩል በማህበር የተደራጁ ቢሆንም  ክፍት የስራ ቦታዎቹ ካሉት የስራ አጥ ብዛት መጠን ጋር ባለመመጣጠኑ ወደ ስራ ለመግባት አለመቻላቸውንም አክለዋል፡፡
ወጣት አማረ ይገዙም ለሶስት ዓመታት በግል ስራ ሲተዳደር ቆይቷል፡፡ በክልሉ ሶስት ዞኖች  በእምነበረድ፣ የድንጋይ ከሰል እና ሌሎችም ዘርፎች በርካታ ወጣቶች ተደራጅተዉ በመጀመሪያ ዙር ባለፈው ዓመት 2012 ዓ.ም 500 የሚደርሱ ወጣቶች  ወደ ስራ የገቡ ሲሆን በክልሉ በኢንቨስትመንት ስራ ለመሰማራት በማህበር ለመደራጀት ጥረትም ቢያደርግም እንዳተሳካለት ተናግረዋል፡፡ በማህበር ተደራጅተው ወደ ስራ ሳይገቡ  ረጅም ጊዜ የሆናቸው ወጣቶች መኖራቸውን አብራርተዋል፡፡
የስራ አጥ ቁርን ለመቀነስ፣ የስራ ዕድል ፈጠራን የማስተባበርና ድጋፍ የማድረግ ሀላፉነት ያለው  የቤኒሻጉል ጉሙዝ ክልል የስራ ዕድል ፈጠራ ኤጀንሲ  በ2013 ዓ.ም ከ32ሺ በላይ ዜጎችን ቋሚና ጊዜያዊ ስራ ለማስያዝ ታቅዶ እደነበር የክልሉ መንግስት የ2013 በጀት ዓመት ሪፖርት መረጃ ያመለክታል፡፡  

Young Graduates in  Benishangul Gumuz Complain of unemployment
ምስል Negassa Desalegn/DW

በክልሉ በእርሻ ኢንቨስትመንት ለመሰማራት መሬት የተሰጣቸው ባለሀብቶችን  በመከታተልና ድጋፍ  ተደረጎላቸውም ወደ ስራ ያልገቡ ባለሀብቶች 51 ሺ 500 በሄክታር መሬት ተመላሽ ተደርገዋል፡፡ ለ116 ሌሎች ባለሀብች የተሰጠ ሲሆን ከዚህም 53ቱ የአካባቢው ነዋሪዎች መሆናቸውን የቤኒሻን ጉል ጉሙዝ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አሻድሊ ሐሰን በክልሉ ምክር ቤት 12 መደበኛ ጉባኤ ወቅት ባቀረቡት ሪፖርት ጠቁመዋል፡፡ ድጋፍ ተሰጥቷቸው ወደ ስራ የማይገቡ ባለሀብቶች ላይ ተከታታይ የሆነ ማስተካከያ እርምጃ በመውሰድ መሬቱን ለሚያለሙ ባለሀብቶች የማዛወር ስራ በስፋት ይሰራል ብለዋል፡፡ ባጠቃላይ ስራ አጥ ወጣቶችን ለመቀነስ በተከናወኑ ስራዎች 20ሺ ለሚበልጡ ዜጎች በ2013 ዓ.ም በጀት ዓመት የስራ እድል መፈጠሩን ርእሰ መስተዳድሩ አስታውቋል። በዘንድሮ ዓመት ለ79 የተደራጁ ማህበራት 49 ሄክትር መሬት መተላለፉም ተገልጸዋል፡፡  በቤኒሻጉል ጉሙዝ ክልል የስራ እድል ፈጠራ ኤጀንሲ መረጃ መሰረት ባለፉት 10 ዐመታት በክልል ደረጃ 72ሺ ስራ አጥ ዜጎች በማህበር በመደራጀትም ሆነ በቅጥር በቋሚና ጊዜዊነት የስራ ዕድል አግኝቷል፡።

ነጋሳ ደሳለኝ

ነጋሽ መሐመድ