1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የምዕራብ ኦሮሚያ የጸጥታ ሁኔታ

ዓርብ፣ ሐምሌ 3 2012

በቄለም ወለጋ ዞን ሚኮ በተባለች ከተማ በሐጫሉ ሁንዴሳ ሞት ሐዘናቸውን ለመግለጽ አደባባይ የወጡ የአካባቢው ነዋሪዎች መንገድ በመዝጋታቸው ከጸጥታ አስከባሪዎች በተፈጠረ ግጭት የአንድ ሰው ሕይወት ማለፉ ተሰምቷል። የዶይቼ ቬለው ነጋሳ ደሳለኝ ትናንት የምሥራቅ ወለጋ የኦሮሞ ፌድራሊስት ኮንግረስ ጽህፈት ቤት ኃላፊ መታሰራቸውን ከፓርቲው አረጋግጧል

https://p.dw.com/p/3f8CJ
Karte Äthiopien Ethnien EN

የምዕራብ ኦሮሚያ የጸጥታ ሁኔታ

ከሁለት ቀናት በፊት በቄለም ወለጋ ዞን ሚኮ በተባለች ከተማ በሐጫሉ ሁንዴሳ ሞት ሐዘናቸውን ለመግለጽ አደባባይ የወጡ የአካባቢው ነዋሪዎች መንገድ በመዝጋታቸው ከጸጥታ አስከባሪዎች በተፈጠረ ግጭት የአንድ ሰው ሕይወት ማለፉ ተሰምቷል። ከድምፃዊው ግድያ በኋላ በምዕራብ ኢትዮጵያ በሚገኙት የኦሮሚያ ከተሞች የሰው ሕይወት ጠፍቷል፤ የአካል ጉዳት የደረሰባቸውም አሉ። የዶይቼ ቬለው ነጋሳ ደሳለኝ በትናንትናው ዕለት የምሥራቅ ወለጋ የኦሮሞ ፌድራሊስት ኮንግረስ ጽህፈት ቤት ኃላፊ መታሰራቸውን ከፓርቲው አረጋግጧል። ነጋሳ በምዕራብ ኦሮሚያ ያለውን ሁኔታ ወደ ስቱዲዮ ከመግባቴ በፊት በስልክ አስረድቶኛል።
ነጋሳ ደሳለኝ
አዜብ ታደሰ