1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

"የኮፒ ራይት ችግር በሥዕሉም ዘርፍ ልጓሙን ወደ ኋላ እየጎተተው ነው" ሠዓሊ ፀጋልደት ተፈራ

ሰኞ፣ ጥቅምት 5 2011

ኅብረተሰቡ ያላወቀው ሥዓሊው ውስጥ የተደበቁ ጥበቦች አሉ። ሠዓሊው የኅብረተሰቡን ችግሮች በሥዕሉ የሚያሳይ ነው ይላል ሠዓሊ ፀጋልደት።

https://p.dw.com/p/36U8d
Äthiopien Addis Abeba junger Maler Tsegalidet Tefera
ምስል privat

የምናብ ፈጠራ ሥዓሊው

አእምሮ የፈጠረው የምናብ ፈጠራ ቀለምና ቡርሹን አዋህዶ ያቀልማል። በወረቀት፣ በእንጨት፣ በብርጭቆ፣ በግድግዳ ላይም ሊሳል ይችላል። በአሸዋ ፣ በሸክላም መጠቀም እንችላለን። በእይታ የሚገለጽ የሚታየውን እንቅስቃሴና ሁኔታ በሥዕል እንዲነበብ ሥዓሊው ሕይወት ይዘራበታል። ምን መግለጽ እንደሚፈልግ ይተርክልናል። ተመልካቹም ሥዕሉን ያነባል። 
ለዓይን ያዝ የሚያደርጉ ደማቅ ቀለማትን በሥዕሎቹ ይጠቀማል። ሥዕል መተዳደሪያ አድርጎታል። ሙሉ ሰአቱ በስነ ጥበብ ሙያ ላይ ትኩረቱን አድርጋል። በአዲስ አበባ ተወልዶ ያደገው ሠዓሊ ፀጋልደት ተፈራ ሥዕልን ከልጅነቱ መሳል እንደጀመረ ይናገራል። 
ቤተሰቦቹ ለሥዕል ሙያው ከፍተኛውን አስተዋጽኦ አድርገውለታል። በአንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት እያለ የክረምት ስልጠናዎችን በተከታታይ ወስዶ ችሎታውን በበለጠ እንዲያዳብር እንደረዳው ይናገራል። 
ኒውራል የአሳሳል ዘዴንም ይጠቀማል። የአሳሳል ዘዴውን የመረጠበት ዋንኛ ምክንያቱ "ኢትዮጵያዊነትን ይገልጽልኛል" ይላል። ኢትዮጵያዊነትን በሥዕሉ ለማንፀባረቅና ኢትዮጵያዊነት እይታ ያላቸውን እየዞረ በማየት በሥዕሉ ለማካተት ይጥራል። 
ሠዓሊው የንግድ ምልክት አርማም ለኤንኤችዋይ ሰርቷል። ይሄንንም እንደስኬት ይቆጥረዋል። 
በሞናክ ሆቴል ለመጀመሪያ ጊዜ በተሳተፈበት ኤግዚቢሽን የሥዕል ሥራዎቹን ለሥዕል አፍቃሪያን ሀ ብሎ ጀምራል። በብሄራዊ ሙዚየምና በኤሊያና ሆቴል ተመሳሳይ መልክ አቅርባል። 
በየአመቱ ሸራተን አዲስ ሆቴል በሚያዘጋጀው "አርት ኦፍ ኢትዮጵያ" ኤግዚቢሽን ላይም ተሳትፋል። እንደ ኢትዮጵያዊያን አቆጣጠር በ2010 በተዘጋጀው የሥዕል ኤግዚቢሽን 60 ሠዓሊያን የተሳተፉበት እንደነበር ገልጾልኛል።
ሥዕሎቹንም ከ3,000 ብር እስከ 50,000 ብር ከዚህ ቀደም እንደሸጣቸውም ነግሮኛል።
ኅብረተሰቡ ያላወቀው ሠዓሊው ውስጥ የተደበቁ ጥበቦች አሉ ይለናል ጸጋልደት። ሠዓሊው የኅብረተሰቡን ችግሮች በሥዓሉ የሚያሳይ ነው ይላልም።
በሙያው ላይ ችግሮች አሉ ይላል። የመሳያ ቀለም እንደልብ አለመገኘቱ በሥዕል ሙያ ላይ ችግር እንደሆነ ይናገራል። ሌላው የኮፒ ራይት ችግር በሥዕሉም ሙያ ዘርፍ ልጋሙን ወደኋላ እየጎተተው እንደሆነና እልባት ሊሰጠው የሚገባው ጉዳይ ነው። 
ሙያውን ለማሳደግ ከቤተሰብና ከትምህርት ቤት መጀመር አለበት እንደፀጋልደት አስተያየት። የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ መምህር የሆነው ሠዓሊ ዮናስ ሀይሉ ከኅብረተሰቡ ጀምሮ እስከ መንግሥት አካል ሊረባረቡበት ይገባል ይላል። እንደችግር የሚያነሳውም ሙያውን ለባለሙያተኛው ባለመተው እንደሆነ ይገልጻል። ሠዓሊ ዳዊት ተፈራም የሰጠኝ አስተያየት በሙያው አልተሰራበትም የሚል ነው። ትልቁን ሚና መጫወት አለበት የሚለውም ቤተሰብ ነው።

Äthiopien Addis Abeba junger Maler Tsegalidet Tefera
ምስል privat

ነጃት ኢብራሂም

አርያም ተክሌ