1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የምስራቅ ወለጋው ግድያ እና አለመረጋጋት

ረቡዕ፣ ኅዳር 28 2015

ዶቼቬለ ከኦሮሚያ ክልል የተለያዩ ከተሞች ያነጋገራቸው ነዋሪዎች መንግሥት በምዕራብ ኦሮሚያ ምስራቅ ወለጋ ዞን ስለተፈጸመው ግድያና ስለተከሰተው አለመረጋጋት በግልጽ እንዲናገር ጠይቀዋል። አስተያየት ሰጭዎቹ መንግሥት አስተዳደራዊ ኃላፊነቱንም በመወጣት ውዥንብሮችን ሊያጠራ ይገባል ሲሉም አሳስበዋል።

https://p.dw.com/p/4Kc97
Äthiopien Vertriebene aus Wollega in Bahir Dar angekommen | Hauptstadt der Amhara-Region
ምስል Alemnew Mekonnen/DW

የሕዝብ አስተያየት፦ የምሥራቅ ወለጋ የጸጥታ ሁኔታ

በምዕራብ ኦሮሚያ ምስራቅ ወለጋ ዞን ስለተፈጸመው ግድያና ስለተከሰተው አለመረጋጋት መንግሥት በግልጽ እንዲናገር ተጠየቀ። ዶቼቬለ ከኦሮሚያ ክልል የተለያዩ ከተሞች ያነጋገራቸው ነዋሪዎች መንግሥት አስተዳደራዊ ኃላፊነቱንም በመወጣት ውዥንብሮችን ሊያጠራ ይገባል ሲሉም ጠይቀዋል፡፡ የአዲስ አበባው ዘጋቢያችን ስዩም ጌቱ ከኦሮሚያ ክልል ከተለያዩ ከተሞች ያነጋገራቸው ነዋሪዎች በተለይም በማህበራዊ መገናኛ ዘዴ በሁለት ፅንፍ የሚሰራጩ መረጃዎች ነዋሪዎችን ግራ ከማጋባትም አልፎ አደገኛ እየሆነ መጥቷል ሲሉ አሳስበዋል። በምስራቅ ወለጋ ዞን ውስጥ ካለፈው ሳምንት ጀምሮ በኪረሙ እና ጊዳ አያና ወረዳዎች በተባባሰው የፀጥታ መደፍረስ በመቶዎች የሚገመቱ ተገድለው በርካቶች ደግሞ ከቀዬያቸው መፈናቀላቸው ነው የሚነገረው፡፡

ሥዩም ጌቱ

ኂሩት መለሰ

አዜብ ታደሰ