1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የሜጀር ጀነራል ክንፈ ዳኘው መያዝ

ማክሰኞ፣ ኅዳር 4 2011

ላለፉት ሰባት ዓመታት ያለ ይፋዊ ጨረታ የ2 ቢሊየን ዶላር ግዢዎችን መፈፀሙ ይፋ የተደረገው የብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ በምሕጻሩ ሜቴክ የቀድሞ ዋና ዳይሬክተር ሜጀር ጀነራል ክንፈ ዳኘው በቁጥጥር ሥር ውለው አዲስ አበባ መግባታቸው ተገልጿል።

https://p.dw.com/p/38BSk
Äthiopien verhaftet 63 wegen Verdachts auf Menschenrechtsverletzungen, Korruption. Der Generalstaatsanwalt Berhanu Tsegaye sagte heute (03.11.2018) lokalen Journalisten, dass die Inhaftierung nach fünf Monaten Ermittlungen erfolgt.
ምስል DW/Y. Geberegziabeher

ሁመራ አካባቢ መያዛቸው ነው የተነገረው

የመቀሌው ወኪላችን ሚሊዮን ኃይለ ሥላሴ የአካባቢ ምንጮቹን ጠቅሶ እንደገለፀልን የቀድሞው ባለስልጣን ከሁመራ ትንሽ ወጣ ካለ ሥፍራ ነው። በወቅቱ አብረዋቸው የመረጃ መረብ ደህንነት ተቋሙ የበላይ ኃላፊ ሜጀር ጀነራል ተክለብርሃን ወልደ አረጋይ የነበሩ ቢሆንም እሳቸው ግን የእስር ማዘዣ ስላልተቆረጠባቸው እንዳልተያዙ እና እንደተመለሱም አክሎ አመልክቷል። ሸዋዬ ለገሠ ተያያዥ ጉዳዮችን አንስታ ከሚሊዮን ኃይለሥላሴ ጋር በአጭሩ በስልክ ተወያይታ ነበር። ሙሉዉን የስልክ ቃለ ምልልስ የድምፅ ማድመጫ ማዕቀፉን በመጫን ይከታተሉ። 

ሚሊዮን ኃይለሥላሴ

ሸዋዬ ለገሠ 

ነጋሽ መሐመድ