1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የማን መሆኑ ያልታወቀዉ መቃብር 

ሐሙስ፣ ነሐሴ 2 2011

በደቡብ ቱኒዚያ ባሕር ዳር አካባቢ የሚኖሩ ዓሣ አጥማጆች የባሕሩ ወጀብ የተፋዉ አስክሬን ማግኘታቸዉ የተለመደ በመሆኑ ሕይወታቸዉን ከባድ እንዳደረገዉ ተናገሩ። አንድ የቱኒዝያ ዓሣ አስጋሪ የሰዉ ልጅ ክብር ይገባዋል በሚል ብቻዉን አስክሬኑን እየለቀመ እዚያዉ ባሕር ዳር መቅበር ቢጀምርም የሚገኘዉ አስክሬን ቁጥር በመጨመሩ ሥራዉ እየከበደዉ ተናግሯል።

https://p.dw.com/p/3NZC7
Tunesien Zarzis | Friedhof der Unbekannten - Ertrunkene Migranten begraben in Djerba
ምስል picture-alliance/dpa/S. Kremer

በባህር ከሰመጡት አፍሪቃዉያን መካከል አብዛኞቹ ከኢትዮጵያና ኤርትራ ናቸዉ

የዶቼ ቬለ «DW» ወኪል የንስ ቦርሸር ቦታዉ ላይ ተገኝቶ እንደዘገበዉ በመርከብ ሜዴተራንያን አቋርጠዉ ወደ አዉሮጳ ለመሻገር ያቀዱና በአደጋ የሰመጡ አፍሪቃዉያን ስደተኞች ፤ አስክሪናቸዉ ደቡብ ቱኒዝያ ባሕር ዳርቻ የባህሩ ወጀብ እየተፋቸዉ አስክሬናቸዉ በየጊዜዉ እንደሚገኝ አመልክቶአል። ይህን ሁኔታ በየጊዜዉ ያጋጠመዉ አንድ የቱኒዝያ ዓሣ አስጋሪ የሰዉ ልጅ ክብር ይገባዋል በሚል አስክሬኑን እየሰበሰበ እዝያዉ ባሕር ዳር መቅበር ቢጀምርም ከጊዜ ወደጊዜ ሜዲተራንያን ባሕር ዉስጥ የሚሰጥመዉ የስደተኛ ቁጥር በመጨመሩ ቀብሩን ብቻዉን ማከናወን ለእሱ እጅግ እንደከበደዉ መናገሩን የ«DW» ወኪል የንስ ቦርሸር ዘግቦአል። ከአፍሪቃ ወደ አዉሮፓ ለመሻገር በጀልባ ሜዲተራንያን ላይ ከሚሳፈሩትና ከሰመጡት ዜጎች መካከል አብዛኞቹ የመጡት ከኢትዮጵያና ኤርትራ መሆኑን የተመድ ዘገባ ያመለክታል።

Tunesien Zarzis | Friedhof der Unbekannten - Ertrunkene Migranten begraben in Djerba
ምስል picture-alliance/dpa/S. Kremer


ይልማ ኃይለሚካኤል
አዜብ ታደሰ 
ኂሩት መለሰ