1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የማሕበራዊ መገናኛ ዘዴዎች ቅኝት

ዓርብ፣ ኅዳር 11 2013

በኢትዮጵያ የፌዴራል መንግስት እና በህወሓት መራሹ ትግራይ ክልል ልዩ ኃይል  መካከል እየተደረገ ያለው  ጦርነት ተጠናክሮ ቀጥሏል።  ሕግን የማስከበር እርምጃ እየወሰድኩ ነው ያለው የፌዴራል መንግስት ድል እያደረገ መሆኑን እየገለጸ ነው።

https://p.dw.com/p/3lc6R
Symbolbild Apps Facebook, Google und Google + Anwendungen
ምስል Imago Images/P. Szyza

የማኅበራዊ መገናኛ ዘዴዎች ቅኝት

በኢትዮጵያ የፌዴራል መንግስት እና በህወሓት መራሹ ትግራይ ክልል ልዩ ኃይል  መካከል እየተደረገ ያለው ጦርነት ተጠናክሮ ቀጥሏል። 

ሕግን የማስከበር እርምጃ እየወሰድኩ ነው ያለው የፌዴራል መንግስት ድል እያደረገ መሆኑን እየገለጸ ነው።በምዕራባዊ እና ደቡባዊ የትግራይ አካባቢዎች የሚገኙትን በቁጥጥር ስር ማዋሉንም የመንግስት ባለስልጣናት አስታውቀዋል።የትግራይ ክልልን የሚያስተዳድረው ህወሓት የተጠቀሱት አካባቢዎች በመንግስት ኃይሎች ቁጥጥር ስር መዋላቸውን ቢያረጋግጥም ጦርነቱ ገና መሆኑን አስታውቋል። ደም አፋሳሹን  ጦርነት በመሸሽ ወደ ጎረቤት ሀገር ሱዳን የተሰዳጆች ቁጥር ከ30,000 መብለጡን የተባበሩት መንግታት ድርጅት ይፋ አድርጓል። 

Tigray-Konflikt | Äthiopisches Militär
ምስል Ethiopian News Agency/AP/picture alliance

ጦርነቱ ካልቆመ የከፋ ሰብዓዊ ቀውስ ሊያስከትል እንደሚችልም አስጠንቅቋል። በእርግጥ ነው ጦርነት አስከከፊም አውዳሚም ነው። ነገር ግን ጦርነቱ በምን አግባብ መቋጫ ማግኘት አለበት በሚለው ላይ ወደ ሁለት ጫፎች የሚለጠጡ ሃሳቦች በማሕበራዊ መገናኛ ዘዴዎች ላይ ሲንሸራሸር  ይስተዋላል። የኢትዮጵያ የፌዴራል መንግስት ህግ የማስከበር ስራ እየፈጸመ መሆኑን እና ህገ ወጦችን ለሕግ ሳያቀርብ ዘመቻውን እንደማያቆም አስረግጦ ገልጿል። ሕወሃት መራሹ የትግራይ ክልል መንግስት በበኩሉ ድርድር እንዲደረግ በተደጋጋሚ እየጠየቀ መሆኑ እየተዘገበ ነው። ይህንኑ ተከትሎ

Äthiopien Pressekonferenz Tigray Defense Forces, Gebre Gebretsdik
ምስል Million Haileselassie/DW

ሳሙኤል ገብሩ የተባሉ በቲዊተር ገጻቸው ላይ ባሰፈሩት መልዕክት «ብዙዎቻችሁ ርህራሄ የሚባል ነገር  አልፈጠረባችሁም። ለራሳችሁ ለመዋጋት በማትደፍሩት እና ለጠባብ የፖለቲካ አላማችሁ ትውልድን በጦርነት ትማግዳላችሁ። በኢትዮ|ጵያ እና ኤርትራ መካከል የተደረገው ጦርነት ያሳደረብን ጠባሳ እኮ ገና አልሻረም። አስከፊነቱን እያንዳንዳችን ምስክርነት መስጠት እንችላለን » ሲሉ ሁለቱንም ተፋላሚ ኃይሎች የተቹበትን መልዕክት አስተላልፈዋል። አቤል የተባሉ  ሰው በተመሳሳይ በቲዊተር ገጻቸው ላይ በጻፉት መልዕክት «ለማንኛውም ነገር ጦርነት መልስ አይሆንም። ስለ ጦርነቱ አስከፊነት መግለጽ የሚችለዉም የገፈቱ ቀማሽ የሆነው የህብረተሰብ ክፍል ብቻ ነው። ልጆቻቸውን ያጡ እናቶች፣ አብሮ አደጎቻቸው የተገደሉባቸው ታዳጊዎች፣ ጧሪ ቀባሪ ያጡ አዛውንቶች ፤ እነርሱ ይናገሩ ። አምባገነኖች እማ ለእነርሱ የጫወታ ያህል ነው። ቅንጣት አይደንቃቸውም ።

እባካችሁ  የህዝባችንን ህይወት  መጫወቻ አታድርጉት » ሲሉ ተማጽነዋል።  ዳንኤል ደሳለኝ የተባሉ አስተያየት ሰጭ በበኩላቸው «ኢትዮጵያ ውስጥ ጦርነት የሚባል ነገር የለም ። ስራው ወንጀለኞችን ለህግ የማቅረብ ህግ የማስከበር ስራ ነው ብላችሁ ሳትፈሩ ዘግቡ። 

ወንጀለኞቹ ከተያዙ ሁሉም ነገር በዛው ሰዓት ይቆማል ። ስለዚህ የትግራይ ህዝብ ለወንጀለኞች ዋሻ መሆንን ትቶ ወንጀለኞቹን ለህግ አሳልፎ ይስጥ። 

እልህ ምንም አይጠቅምም ። ህዝቡ ወጣቶችን እየማገዳቸው ጧሪ አልባ አይሁን ። የትግራይ  ህዝብ የጁንታው ልጆች የት እንደሚኖሩ ማወቅ እንዴት ያቅተዋል ? በስሙ እየተነገደ   ለምን መጠቀሚያ ይሆናል ?» ሲሉ ጥያቄአዊ አስተያየታቸውን ጽፈዋል።

Äthiopien Konflikt Tigray | Grenzort Hamdait, Flüchtlinge
ምስል El Tayaeb Siddig/REUTERS

ስሂርና በሚል መጠርያ የሰፈረ ስንኝ አዘል መልዕክት እንዲህ ይላል። ለአንድ ሃገር ጦርነት ምንም ጥቅም እንደሌለው እንኳን ለዘመናት በጦርነት የኖርን በግጭት ልምድ ያካበትን በመገዳደል ታሪክ ያለን፣ በርካታ የጦርነት ውሎዎችን ያሳለፍን

ይቅርና ለሁለት ሦስት ቀን የሚቆይ ተኩስ መለዋወጥ በራሱ ከፍተኛ የሆነ ጉዳት አለው። ባለ ድል የምንሆን ስለ መሰለን ፣ስለ ጠላነው በለው ስላልን፣ ስለወደድነው ጠብቀው ካልን

ነገሮችን ባርቆ አስተዋይነት፣ በቤተሰብ በወዳጅነት ካልተመለከትነው፤  ሲገፉን ፣በለው ሲሉን ከተነዳን፣ ማስተዋልን ካጣን፣ መቻቻልን እና መቻልን ካሳጣን በክፋት በቂም ቁርሾ እናልቃለን

እንጂ እመነኝ አንሸናነፍም !!!»ብለዋል። ተስፋሁን በቀለ ደግሞ ይህ ጦርነት በማንም አሸናፊነት አይጠናቀቅም

አገሪቱ  ግን አንድ  ሺ ዓመት ወደ ኋላ ይወስዳታል!ሲሉ ስጋታቸውን ገልጸዋል። አቡ ነቢል አብዲ የተባሉ አስተያየት ሰጭ በበኩላቸው « ፖለቲካዊ መፍትሔ የሚባለውን ህወሓት ባለፉት ሁለት ዓመታት አፈር አብልታዋለች። አሁን የሚበጀው ሕጋዊ መፍትሔ ብቻ ነው።» ብለዋል።

በርካታ ቁጥር ያለው ተሰዳጅ ሱዳኑን መጋባቱን በማስመልከት ማርታ የተባሉ በሰጡት አስተያየታቸው

Tigray-Konflikt | Äthiopisches Militär
ምስል Ethiopian News Agency/AP/picture alliance

«ያልታደለ ህዝብ በየዘመናቱ ለስደት ይዳርጉታል ሁሉ ለስልጣን ጥማቱ ለሞሙላት ሲል ይገሉታል ያሳድዱታል ይሄንን ጦርነት ያወጀውም ህዙቡን ለጦርነት የዳረገውም ሁሉም ለሀገር የማይጠቅም ስግብግብ ነው» ብለዋል።

 በሰሞኑ በማሕበራዊ መገናኛ ዘዴዎች በስፋት ከተሰራጩ እና በርካቶች ሃሳባቸውን ካጋሩባቸው ጉዳዮች መካከል የዑጋንዳው ፕሬዚዳንት ዩዌሪ ሙሴቬኒ የፌዴራል መንግስቱን ከትግራይ መስተዳድር ጋር ሊያደራድሩ ነው የሚል ሃሳብ አንዱ ነበር። ምክትል ጠቅላይ ሚንስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚንስትሩ ደመቀ መኮንን ወደ ዑጋንዳ ከመጓዛቸው ቀደም ብሎ የወጣዉ መረጃው ብዙዎች ትኩረት እንዲሰጡበት አድርጎ ነበር። ፕሬዚዳንት ዩዌሪ ሙሳቬኒ በትዊተር ገጻቸው ላይ በፌዴራሉ እና በትግራይ ክልል መንግስታት መካከል ድርድር እንዲደረግ መጠየቃቸው ደግሞ ቀደም ሲል በስፋት ለተሰራጨው መረጃ ጥንካሬ ሰጥቶ ነበር። ነገር ግን ፕሬዚዳንቱ  ከውጭ ጉዳይ ሚንስትር  ደመቀ መኮንን ጋር ከተነጋገሩ በኋላ ድርድር እንዲደረግ የጠየቁበትን ሃሳብ በትዊተር ገጹ ላይ ካሰፈሩት ሃሳብ መካከል ለይተው አውጥተዋል። ይህንኑ ተከትሎም በርካታ አስተያየቶች ተሰጥተውበታል። ዮሐንስ ተሾመ የተባሉ አስተያየት ሰጭ እንዳሉት« ሚስተር ፕሬዝደንት ሊያቁት የሚገባው ጉዳይ በአፍሪካ ሰላም ማምጣትም ሆነ ምጣኔ ሀብቱን ማሳደግ የሚቻለው ሌባን አና ወጀለኛን በእርቅ ሰበብ በስልጣን ላይ ማቆየት አይደለም ፡፡ ይልቁንም የህግ የበላይነትን በማረጋገጥ ወደድሞክራሲያዊ ስርአት በመጓዝነው ልማትም ሰላምም ማረጋገጥ የሚቻለው።»ብለዋል። ነባይ ዘለቀ ዘውዴ ደግሞ

ሚስቱ ከፊት-ለፊቱ "በቡድን!" የተደፈረችበትን፣ ልጆቹ ከትምህርት ገበታቸው የታገቱበትን፣ ወንድሞቹ ያለ ጥፋታቸው የታረዱበትን፣ ቤተ-እምነቶቹ ያለርህራሄ የጋዩበትን፣ "በላቡ!" ያፈራው የእድሜ-ልክ ጥሪቱ የተዘረፈበትን፣ "ያለስሙ!" ክፉ-ስም ተሰጥቶት ተገፍቶ አንገቱን የደፋውን..... እነዚህና የመሳሰሉ በርካታ የግፍ ሸክሞች አጉብጠው የሰበሩትን ሰው/ህዝብ እንደው እንደዋዛ "ድርድር፣ ይቅርታ፣ ምናምን..." እያላችሁ ለምታላዝኑበት ሁሉ በአጭሩ የምላችሁ አለኝ፦

እናንተ "ይቅርታ" ምን እንደሆነ እንኳ የማታውቁ፣ ሞባይል ለሚነጥቃችሁ ምስኪን እንኳ "እሪ... ካልገደልኩት ኮረንቲ እጨብጣለሁ!" የምትሉ፣ በሌሎች መሪር እምባና ደም የምትነግዱ "ክፉ መሰሪዎች!" ናችሁ።» ብለዋል።

ዴቭ ግርማይ  «ድርድር አያስፈልግም ህዝብና እውነትን የያዘ ወገን ያሸንፋል።» ሲሉ አለማየሁ ወርቅነህ ደግሞ «መደራደር አንደሽንፈት መቆጠር የለበትም ከጦርነት ሰላም ይሻለልና ከሰላም ብዙ ነገር ይገኛልና»

ቤዩ ሐዋሳ የተባሉ አስተያየት ሰጭ በበኩላቸው « አንድ መሪ የራሱ የሆነ አቋም ሊኖረው ይችላል ነገር ግን አሳምኖ ማስለወጥ ይህ አንዱ የዲፕሎማቲክ ውጤት ነው መሪያችን በርታ! » የሚል አስተያየት አስፍረዋል።

Äthiopien Konflikt Tigray | Milizen der Amhara-Region
ምስል Tiksa Negeri/REUTERS

በባህር ዳር  ከተማ ላይ ዛሬ ሌሊት ላይ ለሁለተኛ ጊዜ የሮኬት ጥቃት መፈጸሙን የአማራ ክልል መንግስት አረጋግጧል። ይህ ዝግጅት እስከተሰናዳበት ጊዜ ድረስ ስለደረሰ ጉዳት የተባለ ነገር የለም። የትግራይ ክልል በበኩሉ የፌድራሉ መንግስት በመቀሌ ዩኒቨርሲቲ ላይ የአየር ጥቃት መፈጸሙን እና  በተማሪዎች ላይ ጉዳት መድረሱን አስታውቋል። የትግራይ ልዩ ሃይል በባህር ዳር እና በጎንደር ከተሞች ካደረሰው የሮኬት ጥቃት ባሻገር ቀደም ሲል በኤርትራ መዲና አስመራ ላይ ተመሳሳይ ጥቃት መፈጸሙ ድርጊቱ አለማቀፋዊ ይዘት እንዲኖረው ታስቦ የተደረገ ነው በማለት አንዳንድ የምዕራቡ አለም መንግስታት ድርጊቱን ኮንነውታል። ጀርመን ፣ ስጳኝ እና ዩናይትድስቴትስ ድርጊቱን አጥብቀው ከተቃወሙ ሀገራት ውስጥ ተጠቃሾች ናቸው። ይህንኑ በተመለከተ የማህበራዊ መገናኛ ዘዴ ተከታዮች እንዲሁ  በመደገፍም ሆነ በመቃወም አስተያየቶቻቸውን አጋርተዋል።  

ታምራት ዲንሳ

አዜብ ታደሰ