1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የማሊ ፕሬዚደንታዊ ምርጫ ዝግጅት  

ዓርብ፣ ሐምሌ 20 2010

ውጥረት ባልረገበባት ማሊ የፊታችን እሁድ ፕሬዚደንታዊ ምርጫ ይካሄዳል። በዚሁ ምርጫ ከወቅቱ የሀገሪቱ ፕሬዚደንት ኢብራሂሚ ቡባከር ኬይታ ጎን 23 ዕጩዎች ይወዳደራሉ። አዲስ የሚመረጠው ርዕሰ ብሔር  ብዙ ተግዳሮቶች ይጠብቁታል።

https://p.dw.com/p/32Dcx
Mali Wahl in Mali 2018 | Wahlplakate
ምስል DW/K. Gänsler

Vorbericht Mali Wahlen - MP3-Stereo

በደቡብ ማሊ በሲካሶ ከተማ የደጋፊዎች ድምጽ ለማሰባሰብ ዘመቻ ያደረጉት ሼክ ሞዲባ ዲያራ  ከ2012 ዓም መፈንቅለ መንግሥት በኋላ የተቋቋመው የሽግግር መንግሥት ጠ/ሚ ነበሩ። ሴይዱ የናሳ ባልደረባ የነበሩት የዲያራ ደጋፊ ነው። በዲያራ ላይ ትልቅ ተስፋ አሳድሯልረዋል።
« ወደ ምርጫ ጣቢያ የምሄድ ከሆነ ድምፄን ለሼክ ሞዲባ ዲያራ ነው የምሰጠው። በኔ አስተያየት፣ ዲያራ ለውጥ የሚያመጡ ዕጩ ናቸው። በፖለቲካው መድረክም ላይ አዲስ ገጽ ናቸው። ብዙ ሀሳቦች አሏቸው። የስራ ቦታ፣ የሙያ ስልጠና ወይም ለሌሎች ወቅታዊ የሀገሪቱ ችግሮች መፍትሔ ማፈላለጉ አይከብዳቸውም ብየ አስባለሁ። »

በማሊ ስራ አጥነት ትልቅ ችግር ነው። እጥረት አለ። በተመድ የሰብዓዊ ልማት ደረጃ ላይ ማሊ ከ188 ሀገራት ውስጥ 175ኛ ነች። ከሀገሪቱ 18 ሚልዮን መካከል በተለይ ወጣቱ 66%  የሚሸፍን ሲሆን፣ ከ25 ዓመት በታች የሆነው ወጣት በስራ ቦታ  እጥረት እና በብሩህ እድል ማጣት አዘውትሮ ቅሬታውን  ያሰማል። ይህ የቅሬታ ስሜት ባንዳንድ የማሊ አካባቢ ከፍተኛ  መሆኑን ይህን በተመለከተ ከጥቂት ጊዜ በፊት የሕዝብ አስተያየት መመዘኛ መዘርዝር ያወጣው በማሊ የሚገኘው ፍሪድሪክ ኤበርት ሽቲፍቱንግ የተሰኘው የጀርመናውያኑ የፖለቲካ ጥናት ተቋም ኃላፊ ፊሊፕ ጎልድበርግ ገልጸዋል።
« ይህ የአስተያየት መመዘኛ መዘርዝር በተለይ ወጣቱ በፖለቲካው አኳያ እምነት እንደሌለው ያሳያል። ይህ ስሜት በመዲናይቱ ባማኮ ብቻ ሳይሆን፣ ሲካሶን እና ኬይስን በመሳሰሉ ያካባቢ ግዛቶች  ከተሞችም  ተስተውሏል።»
ያም ቢሆን ግን ፕሬዚደንት ኢብራሂም ቡባከር ኬይታ ከሌሎች 23 ዕጩዎች ጋር ለድጋሚ ምርጫ ለመወዳደር በመወሰን ፣ የምርጫ ዘመቻቸውን አጠናክረው በማካሄድ ላይ ይገኛሉ። ከ2012 ዓም መፈንቅለ መንግሥት እና አክራሪ ሙስሊም ቡድኖች ሰሜናዊ ማሊን ለብዙ ወራት ከያዙ በኋላ በ2013 የተመረጡት ፕሬዚደንት ኬይታ ሀገሪቱን የማረጋጋት እና እርቀ ሰላም የማውረድ ከባድ ስራ ነበር የጠበቃቸው።
ይኸው ስራቸው እንዲሳካ በመርዳቱ ተግባር ላይ በሀገሪቱ የተሰማራው በምህጻሩ ሚኑስማ የተባለው እና 13,300 ወታደሮች ያሰለፈው የተመድ ሰላም አስከባሪ ጓድ ድርሻ እንዳለው ይታመናል። ብዙዎች የፀጥታው ሁኔታ ስጋት በሚታይባት በማሊ ምርጫ ማድረግ ካለሚኑስማ ድጋፍ እውን ይሆናል ብለው አያስቡም። 

Mali Wahl in Mali 2018 | Anhänger von Cheick Modibo Diarra in Sikasso
ምስል DW/K. Gänsler

ሚኑስማ አደገኛ በሚባሉ ኪዳል እና ቲምቡክቱን ወደመሳሰሉ ከተሞች በመሄድ የምርጫ ቅስቀሳ ለማድረግ ለሚፈልጉ ተወዳዳሪዎች በአይሮፕላኑ ለማድረስ ሀሳብ እንዳቀረበ ተሰምቷል፣ ይሁንና፣ በምርጫው ዝግጅትም ሆነ ፀጥታ በማስከበሩ ተግባር ውስጥ እንደሌለበት የጓዱ ኃላፊ ማርቲን ናዶ ተናግረዋል።
ፕሬዚደንት ኬይታ በባማኮ ባደረጉት የምርጫ ዘመቻ ወቅት ስለሚከተሉት መርሀግብር ገለጻ አድርገዋል፣ ብዙዎች ገለጻው ባለፉት አምስት ዓመታት የሰሩትን ባጭሩ የተናገሩበት እንደነበር የተናገሩት። 
« ሀገሪቱ የምትገንበት ሁኔታ ከአሁን ቀደም ከነበረው ጋር በፍጽም አይመሳሰልም። የያኔዎቹ ችግሮች አሸንፈናቸዋል።, »
በመንገድ ግንባታ ፣ እንዲሁም፣ ከሀገሪቱ ብሄራዊ ጠ/ገቢም 40% በሚሸፍነው ያስገኙትን ስኬት ዘርዝረዋል።  ይህ ግን ለድጋሚ መመረጥ ያበቃቸዋል ሲሉ ብዙዎች ይጠይቃሉ። 
የመራጮች ምዝገባ በጣም አዝጋሚ ነው። የተቃዋሚው ወገን ዕጩ ሱሌይማን ሲሴ እንደሚሉት፣ ሁለት የተለያዩ የመራጮች ዝርዝሮች አሉ። አንደኛው ዝርዝር  ከ1,2ሚልዮን የሚበልጡ የሌሉ  መራጮች ስም ይዟል። በማሊ መንግሥት ዘገባ መሰረት፣ 8,2 ሚልዮን የመምረጥ መብት ያላቸው ዜጎች አሉ። በሀገሪቱ በሚታየው የፀጥታ ስጋት  የተነሳ፣ በተለይ በሰሜናዊ ማሊ የፊታችን እሁድ በሚካሄደው ምርጫ ላይ ምን ያህል  መራጭ እንደሚሳተፍ ከወዲሁ መግመት አዳጋች ነው። ያም ቢሆን ግን፣ የሼክ ዲያራ ደጋፊ እና  የሲካሶ ከተማው መራጭ ሴይዱ የምርጫ ዕለት ወደ ምርጫ ጣቢያ በመሄድ ድምፁን እንደሚሰጥ አመልክቷል። ይሁንና፣ ይላል ሴይዱ፣ በመጨረሻ ማሊን ወደፊት ማራመድ ያለበት ሕዝቡ ነው። »
በእሁዱ ምርጫ አንዱም ተወዳዳሪ ካላሸነፈ ነሀሴ 12፣ 2018 ዓም የመለያ ምርጫ ይደረጋል። 

አርያም ተክሌ / ካትሪን ጌንስለር  

ነጋሽ መሐመድ