1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የማህበራዊ መገናኛ ዘዴዎች ቅኝት 

ዓርብ፣ ጥር 15 2012

ሰሞኑን በማህበራዊ መገናኛ ብዙሀን ሲያነጋግሩ ከነበሩት ጉዳዮች መካከል የህዝባዊ ወያኔ ሐርነት ትግራይ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባል የወይዘሮ ፈትለወርቅ ገብረ እግዚአብሔር ከንግድ እና ኢንዱስትሪ ሚኒስትርነት መነሳት አንዱ ነው። የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ትናንት ያቀረበው ዘገባም ሌላው አነጋጋሪ ርዕስ ነበር።

https://p.dw.com/p/3WmlD
Emblem der Tigray People's Libration Font (TPLF)

የጥር 15ቀን 2012ዓም ማህበራዊ መገናኛ ዘዴዎች ቅኝት

በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ካቢኔ ብቸኛዋ የህወሓት ማዕከላዊ ኮሚቴ አባል የነበሩት ወይዘሮ ፈትለወርቅ ከሚኒስትርነታቸው መነሳታቸው በዚህ ሳምንት ይፋ ከተደረገ በኋላ ህዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ ህወሓት ባወጣው መግለጫ አባላቱ ከፌደራል መንግሥት ሹመት መነሳታቸውን በፍጹም ተቀባይነት የሌለው ሲል ተቃውሟል።ሹም ሽሩ እና ተከትሎት የወጣው የኢህአዴግ መግለጫ በማህበራዊ መገናኛ ብዙሀን ልዩ ልዩ አስተያየቶች ተሰጥተውበታል። አሌክስ ኃይሉ በሚል ስም የፌስ ቡክ ተጠቃሚ «በግልፅ ተቃዋሚነቱን ያሳየ እንዴት አብሮ ይሰራል_? ሲሉ አስተያየታቸውን በጥያቄ ይጀምራሉ።እስከዛሬም በፌደራል ስልጣን ውስጥ መኖራቸው አጠያያቂና አስጊም ጭምር ነው። ፅዳቱ ወደታች ወደወረዳም ይውረድ,,,ካሉ በኋላ«,ነገር ግን ከሕወሐት ጋር ንክኪ የሌላቸውን ታታሪ ሠራተኞችም አብረው እንዳይጎዱ የማጥራቱ ስራ በጥንቃቄ ይቀጥል ሲሉ መክረዋል። 
«በርዕዮት አለም የማይመሳስሉ አካላትን ወደ ስልጣን አለማምጣት ያሰተማረው ህወሓት ነው እስከ ዛሬ በአስተሳስብ የተለያዮ የፖለቲካ ፖርቲዎች በሃላፊነት ሲመሩ አላየንም ብልፅግናም ይህንን ነው የተከተለው ለኛ ሲሆን ይስራ የሚል አማርኛ ተቀባይነት የለውም፡፡»ያሉት ደግሞ ቴዎድሮስ በላይ ናቸው።«በራስ ሲደርስ እንዲህ ያማል !!!ምናለ ዝም ብላችሁ የዘራችሁትን ብቻጭዱ»በማለት አስተያየታቸውን በአጭሩ ያሰፈሩት ደግሞ ወዳጄ ኢዘዲን ናቸው።ቴዲ ቴዲ የተባሉ የፌስ ቡክ ተጠቃሚ ከአሁኑ የባሰ ሰላም አጥተን አናውቅም ግን ከስልጣን ማባረር መፍትሄ ሆኖ አያውቅም ነገሮች ከእለት ወደ እለት እየባሱ ነው ያሉት ቅድሚያ እስኪ በሰላም ስሩ።» በማለት ሃሳባቸውን ገልጸዋል።ደሱ የአወቀ ልጅ ነኝ በሚል የፌስ ቡክ ተጠቃሚ «አይ ጊዜ መሰላሉ አንዱ ሲወጣ አንዱ ይወርዳል!»ብለዋል ኡዴሳ ጊርጃ ደግሞ«ከወደቁ በኋላ መንፈራገጥ ለመላላጥ ነው።ምንም የሚፈጠር ነገር የለም።ብለዋል።የመንጋ ዘመን ፖለቲካ በሚል ስም የሰፈረ አስተያየት «ከአስተያየት ሰጪዎች ለመረዳት እንደሞከርኩት ከሆነ የአብዛኛው ሰው አስተያየት አመዛዝኖ ከመፍረድ ይልቅ አንድ ፅንፍ የያዘ፡እንኳን ህወሓትን፣እንኳን የትግራይ ተወላጅ የሆኑ ሰዎችን ይቅርና በእኩልነት የሚያምንን ሁሉ ያስተዛዝባል።ይላል።ጀምበሬ አያና ምትኩ ብልፅግና ፓርቲን ካልተቀበላችሁ ስልጣን በፌደራል ደረጃ ምን ይሰራላችኋል የምትቃወሙ ህወሀቶች? ሲሉ ሃሳባቸውን በጥያቄ አርበዋል።ህወሓት የከትናንት በስተያውን ሹም ሽር በተቃወመበት መግለጫው « በማንአለብኝነት ህዝብ ያልመረጠው ሌላ አዲስ ድርጅት ሥልጣን እንዲይዝም ሆነ አገር እንዲመራም ማድረግ የህዝቡን ስልጣን መቀማትና ህገ መንግስቱን መርገጥ ነው። ሀገር እንዲመራ በጋራ ለተሰጠን ሃላፊነት በተወሰኑ ኃይሎች ፍላጎት ሕጋዊና ዴሞክራሲያዊ ያልሆኑ ውሳኔዎች ሊወሰኑና ሊተገበሩ አይገባም።»ብሏል 
ፊሽ ሚኪ በዚህ አባባል ላይ ጥያቄ አንስተዋል። ለነሱ ሀገር እንዲመሩ ሃላፊነት የሰጠ ማን ነው? ትህነግ በጉልበት እንጅ በዲሞክራሲ 27 አመት እንዳልገዛ ማንም ያውቃል ታዲያ ህዝብ የሰጠንን ሃላፊነት ማለት የመቼውን ነው? ጠይቁልኝ።ሲሉ ሚፍታ ጀማልም ተመሳሳይ ጥያቄ አቅርበዋል። ማነው? መች ነው? የት ነው? ህዝብ ሃገር እንዲመሩ አደራ የሰጣቸው? በግድ በሃይል በሚል ይስተካከል።በማለት።ምናልባት ሹም ሽሩ ሚ/መስሪያ ቤቱን በደንብ ካለመምራት የተወሰደ ከሆነ ባይከፋም፤ከሀገራዊ አድምታዉ ብስለት የጎደለዉ ስሜታዊ እርምጃ ይመስላል።ሲሉ ሃሳባቸውን የገለጹት ፈልሜታ ገዳ «የኢትዮጵያን አንድነት አስጠብቃለሁ ብሎ ከሚል መሪ አይጠበቅም ይቺን አጭር ወራት ቢታገስ መልካም ነበር"ልጅ ያቦከዉ ለራት አይበቃም"በማለት ሃሳባቸውን ደምድመዋል። ናድሂ አባጂፋርም ብልጽግና መቼ ስልጣን ይዞ ነው ህዋሀት ኢህአዴግን ከስልጣን የሚያባርረው አሁንም ስልጣን ላይ ያለው መንግስት በኢህአዴግ ስም መሆኑን መታወቅ አለበት ስለዚህ ይሄ የምርጫ ጊዜ እስኪያልቅ ገዢ መንግስት የሚባለው ኢህአዴግ ነው።ሲሉ ሚኒስትሯ መሻራቸው ትክክል እንዳይደለ ለማስረዳት ሞክረዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በዚህ ሳምንት መጀመሪያ ላይ ከሾሟቸው ሶስት አዳዲስ ሚኒስትሮች ወይዘሮ ፈትለወርቅን የተኩት  አቶ መላኩ አለበል ናቸው። ከአቶ መላኩ ሌላ ዶክተር ኢንጅነር ጌታሁን መኩሪያ የትምህርት ሚኒስትር፣  ዶክተር አብርሃም በላይ የኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ሆነው ተሾመዋል።
አብይ ያደረገው መልካም ሆኖ ሳለ ነገር ግን አንዳንዶች ደግሞ ሌሎችም የህውሀት አባል መነሳት አለባቸው የምትሉ ግለሰቦች ከጭፍን ጥላቻ መውጣት ይበጀናል፣ መልካም የሚሰሩትን ማበረታታት እንጂ በጭፍን ሁሉንም መጥላት ተገቢ አይመስለኝም ያሉት ደግሞ ዩሱፍ ኢብራሂም ናቸው። 
የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ትናንት ለኢትዮጵያ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ያቀረበው ያለፉት ስድስት ወራት የስራ ክንውን ዘገባ በማህበራዊ መገናኛ ዘዴዎች ብዙ አስተያየቶች ተሰጥውበታል።ኮሚሽነሩ ዶክተር ዳንኤል በቀለ ለምክር ቤቱ ባቀረቡት ሪፖርት ለውጡ ውስብስብ ባሏቸው ተግዳሮቶች እና እንቅፋቶች ሰበብ የሰብዓዊ መብት ቀውስ እንደገጠመው ገልጸዋል።በብሄርና በሃይማኖት ሰበብ የተካረሩ ፖለቲካዊ ማህበራዊ እና ኤኮኖሚያዊ ቀውሶች የአመጽ ግጭት እየቀሰቀሱ በከተማም በገጠርም በጎዳናም በመንደርም፣ በሆስፒታሎችና ትምህርት ተቋማት ሳይቀር ዜጎች በአሰቃቂ እና አስነዋሪ መንገድ መገደላቸውን፣ መደፈራቸውን፣ የአካል ጉዳት ሰለባ መኾናቸውን፣ ከመኖሪያቸው፣ ከሥራቸው፣ መፈናቀላቸውን እንዲሁም በርካታ የሕዝብና የሀገር ንብረት መውደሙን ገልጸዋል።ቁጥር እና ቦታን ሳይጠቅስ በጥቅል የቀረበው ይህ ዘገባ ልዩ ልዩ ትችቶች ተሰንዝረውበታል።ፈልመታ ገዳ የተባሉ የፌስ ቡክ ተጠቃሚ ዝርዝር ዘገባ መቅረብ አለበት መቼ የት በማን የሚሉትን በተብራራ መልክ ማቅረብ ሲገባ የተዳፈነ ዘጋባ ወንጀለኛዉ እንዲበሰበስ ያደርጋልል። ለማረምም ዕድል የሚፈጥር አይዴለም በማለት ተችተዋል።አቶ ዳንኤል ሲሉ የሚጀምሩት ጥላቻን ነቅፌ ፍቅርን ደግፌ በሚል የፌስቡክ ስም አስተያየት ሰጭ የችግሩን ፈጣሪዎች 123 ብሎ ማስቀመጥ አልተቻለም ማለት ነው? በማደባበስ መፍትሄ ይገኝል ብለው ያምናሉ? የጅምላ ፍረጃ ወንጀለኛውን ማጀብ እንጂ ለተጠያቂነት ማጋለጥ አይደለም! ይታሰብበት! ካሉ በኋላ አነሰም በዛም የአደባባይ ሚስጥሩን ነካ አድርገው በማለፍዎ እናመሰግናለን! ብለዋል።ሲሳይ ወያኔ ትግራይ በሚል ስም ይህ ግን እኮ የፖሊስ ኮሚሽን ሪፖርት ነው። የተለየ ስራ እና ሃላፊነት ከሌለው የሰብአዊ መብት ኮሚሽን ማቋቋም ለምን አስፈለገ?ሲሉ ሃሳባቸውን በጥያቄ ይደመድማሉ።ሪፖርቱ ትንናት ከቀረበላቸው የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላትመካከል ዘገባውን የሀገሪቱን ተጨባጭ የሰብዓዊ መብት ጥሰት ያልዳሰሰ  ፍርሃት የተጫነው እና ችግሩን በአግባቡ የማያሳይ ሲሉ ያጣጣሉም አሉ ዳዊት ይርጋ የተባሉ የፌስቡክ ተጠቃሚም ተመሳሳይ ትችት አቅርበዋል ። ደካማና እንደው አለሁ ለማለት ለይስሙላህ የቀረበ ድፍረት የሌለው ሪፖርት ሲሉ።ተሬ አየሉ ተጠያቂዎቹ እራሳቸውን በአግባቡ ሳይመሩ ህዝብ እንመራለን ባይ አላዋቂዎች ናቸው መንግስት እነዚህን መስመር ካልያሳዘ አገሪቱ አትረጋጋም ብለዋል። 
 አሁን ስላለፈው ማውራቱ ምንም መፍትሄ ሊሆን አይችልም፤ያሉት ራሂመት ያሲን ደግሞ ለወደፊቱ ምን ይሁን የሚለው ላይ ትኩረት ማደረጉ አይሻልም ?ብለው ለፌስ ቡክ ተከታታዮች ሃሳብ አቅርበዋል። 
ኂሩት መለሰ

Äthiopien Daniel Bekele
ምስል DW/S. Muchie
Repräsentantenhaus in Äthiopien
ምስል DW/Y. Gebreegiziabher

ነጋሽ መሐመድ