1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የመጋቢት 03/2013 ዋና ዋና ዜናዎች

ዓርብ፣ መጋቢት 3 2013

በመላው ዓለም አፋጣኝ እርምጃ ካልተወሰደ የኮሮና ወረርሽኝን ጨምሮ በረሃብ እና የአየር ንብረት መዛባት የብዙ ሚሊዮን ሰዎችን ሕይወት ሊቀጥፍ እንደሚችል የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ጸሐፊ አንቶኒዮ ጉተሬዝ አስጠነቀቁ።

https://p.dw.com/p/3qZ6P

በመላው ዓለም አፋጣኝ እርምጃ ካልተወሰደ የኮሮና ወረርሽኝን ጨምሮ በረሃብ እና የአየር ንብረት መዛባት የብዙ ሚሊዮን ሰዎችን ሕይወት ሊቀጥፍ እንደሚችል የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ጸሐፊ አንቶኒዮ ጉተሬዝ አስጠነቀቁ። በዓለም ከሰላሳ የሚልቁ ሃገራት ከ30 ሚሊዮን በላይ ህዝብ በረሃብ መጠቃታቸውን ይፋ ለማድረግ ከጫፍ መድረሳቸውን ጉተሬዝ አስታውቀዋል።

በናይጄሪያ በሳምንታት ጊዜ ውስጥ ታጣቂዎች በ30 ተማሪዎች ላይ ሌላ እገታ ፈጸሙ። ታጣቂዎቹ በሰሜናዊ ምዕራብ ናይጄሪያ የሚገኝ አንድ ትምህርት ቤትን በመውረር ዕገታውን እንደፈጸሙ የአካባቢው ባለስልጣናት አስታውቀዋል።

ቱርክ ከጎርጎርሳውያኑ 2013 በኋላ ለመጀመርያ ጊዜ ከግብጽ ጋር ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ማድረጓን አስታወቀች። ግንኙነቱን ወደ ተሻለ ምዕራፍ የማድረስ ፍላጎት እንዳላት አንካራ ዛሬ ይፋ አድርጋለች።

ባለፈው የጎርጎርሳውያኑ 2020 በመላው ዓለም 65 ጋዜጠኞች በስራቸው ላይ እያሉ መገደላቸውን ዓለማቀፉ የጋዜጠኞች ፌዴሬሽን አስታወቀ። ግድያው በ 16 ሀገራት ውስጥ ሲፈጸም ግድያዎቹ ታቅደው የተፈጸሙ እና የቦምብ ጥቃትን ጨምሮ ግጭቶች በተቀሰቀሱ አካባቢዎች በተባራሪ ጥይቶች የደረሱ ናቸው ተብሏል።