1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

«የመገናኛ አውታሮች ሚና በኢትዮጵያ ቀጣዩ ምርጫ»

እሑድ፣ ሰኔ 6 2013

መገናኛ አውታሮች፦ ጥላቻ እና ግጭትን በማራቅ በኅብረተሰቡ ዘንድ መቀራረብ እና መተማመን እንዲሰፍን፤ ምርጫውም በሰላማዊ መንገድ እንዲጠናቀቅ ምን እያደረጉ ነው፤ ምንስ ማድረግ ይጠበቅባቸዋል?

https://p.dw.com/p/3uofR
Symbolbild Onlinejournalismus Online-Journalist
ምስል Fotolia

ከመገናኛ አውታሮች ምን ይጠበቃል?

ኢትዮጵያ ስድተኛውን ሀገር አቀፍ ምርጫ ለማካኼድ ዝግጅቱን በማጠናቀቅ ላይ ትገኛለች። ለአንድ ሀገር ዴሞክራሲ ማበብ ወሳኝ ከኾኑ ዐበይት ጉዳዮች መካከል ምርጫ አንዱ ነው። ምርጫን በተገቢ መንገድ ለማከናወን ደግሞ የመገናኛ አውታሮች ሚና ወሳኝነት አያጠያይቅም። ፍትኃዊ እና ነጻ ምርጫ ለማካኼድ የበይነ መረብም ኾኑ መደበኛ የሚባሉት የመገናኛ አውታሮች ድርሻ እንዲህ በቀላሉ የሚታይ አይደለም። በእርግጥ መገናኛ አውታሮቹም ኾኑ የሀገር ውስጥ እና የውጭ ሃገራት ጋዜጠኞች በምርጫው ላይ የሚያንጸባርቁት በአወንታዊም በአሉታዊ ጎኑም ሊገመገም ይችላል።

የኢትዮጵያ ምርጫ በሰላማዊ መንገድ እንዲጠናቀቅ ጥንቃቄ እያደረጉ በተገቢው መልኩ የሚዘግቡ በርካቶች ናቸው።  በዚያው መጠን አቅጣጫ እና አጀንዳ መስጠት፣ በፖለቲካ አመለካከት፣ በጎሳ እና በጥቅም እንዲሁም በሌሎች ጉዳዮች የሚቃወሟቸውን ወገኖች ማብጠልጠል፤ ብሎም መሠረት የሌላቸው ውሸቶች ማሰራጨት ላይ የተጠመዱም በርካቶች ናቸው።

መገናኛ አውታሮች፦ ጥላቻ እና ግጭትን በማራቅ በኅብረተሰቡ ዘንድ መቀራረብ እና መተማመን እንዲሰፍን፤ ምርጫውም በሰላማዊ መንገድ እንዲጠናቀቅ ምን እያደረጉ ነው፤ ምንስ ማድረግ ይጠበቅባቸዋል?«የመገናኛ አውታሮች ሚና በኢትዮጵያ ቀጣዩ ምርጫ»፦ የእንወያይ መሰናዶዋችን የሚያጠነጥንበት ርእሰ ጉዳይ ነው። በውይይቱ 3 እንግዶች ተሳታፊ ናቸው። 

ማንተጋፍቶት ስለሺ

ነጋሽ መሐመድ