1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የመካከለኛው ምሥራቅ ፍጥጫ እና አፍሪቃ

ሐሙስ፣ ታኅሣሥ 30 2012

በኢራን እና ዩናይትድ ስቴትስ መካከል የተካረረው ውዝግብ ካለፈው ሳምንት ወዲህ መልኩን ቀይሮ ወደኃይል ርምጃና የበቀል ምላሽ መሸጋገሩ በመካከለኛው ምሥራቅ ውጥረቱን አባብሶታል። በመካከለኛው ምሥራቅ የተካረረው ጉዳይ ጦሱ አፍሪቃም ይተርፋት ይሆን?

https://p.dw.com/p/3Vwnq
Raketenangriffe auf Stützpunkte im Irak | US-Militärstützpunkt Ain al-Assad
ምስል picture-alliance/dpa/N. Nasser

«ጦሱ አፍሪቃም ይተርፋት ይሆን?»

በኢራን እና ዩናይትድ ስቴትስ መካከል የተካረረው ውዝግብ ካለፈው ሳምንት ወዲህ መልኩን ቀይሮ ወደኃይል ርምጃና የበቀል ምላሽ መሸጋገሩ በመካከለኛው ምሥራቅ ውጥረቱን አባብሶታል። ኢራን የተገደሉባት ጄነራሏን አፈር ባለበሰች ዕለት ሌሊቱን በኢራቅ ባሉ የአሜሪካ የጦር ሰፈሮች ላይ ያወረደችው የሮኬት ናዳ ያደረሰው የጉዳት መጠን እስካሁን ይፋ ባይሆንም የነዳጅ ዋጋ መናሩ እየተነገረ ነው። የሁለቱ ወገኖች ፍጥጫ እና አቅም መፈታተሽ አዝማሚያው ያሰጋቸው ሃገራት እና ተቋማት ውጥረቱ እንዲረግብ እየጠቀዩ ነው። የተመድ በእጅ አዙር የጦር አውድማ በሆነችው ኢራቅ ላይ የሚካሄደው ጥቃት እና የአፀፋ ርምጃ ሀገሪቱን ዳግም ችግር ውስጥ እንዳይጥል ጥንቃቄ እንዲደረግ አሳስቧል። በመካከለኛው ምሥራቅ የተካረረው ጉዳይ ጦሱ አፍሪቃም ይተርፋት ይሆን? ይህንና ተያያዥ ነጥቦችን በማንሳት አዜብ ታደሰ ፤ በመቀሌ ዩንቨርስቲ የፖለቲካ ሳይንስ ምሁሩን ረዳት ፕሮፌሰር የማነ ዘርዓይን አነጋግራለች። 

አዜብ ታደሰ

ሸዋዬ ለገሠ